(ቢላል)፦ በቅርቡ በአሰንዳቦ ከተማ አከባቢ በቀርሳ፣በኦሞናዳ፣ በጥሮ አፈታ ወረዳዎች የጴንጤ ቤተክርስቲያኖች ተቃጠለ በተባለበ ሁኔታ ከ100 በላይ ሙስሊሞች ላይ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጠ፡፡
ሰሞኑን በተለያዩ ቀናት በሰጠዉ በዚህ የፍርድ ዉሳኔ መሰረት አብዛኛዎቹ ከአራት ዓመት እስከ ስምንት ዓመት የተፈረደባቸዉ ሲሆን እንዲሁም 16፣14፣12 እና 10 ዓመት እስራት የተፈረደባቸዉም ይገኙበታል፡፡
የአካባቢዉ ምንጮች እንደገለጹልን ከፍተኛዉ ፍ/ቤት ሰዎቹ በዋስ እንዲለቀቁ ቢልም ወረዳ ፍ/ቤቶቹ ይህንን ያለመቀበላቸዉና ህብረተሰቡ ገንዘብ በማዋጣት የጠፋዉን ለመተካት ጭምር በሚሯሯጥበት ጊዜ ነዉ ይህ ቅፅበታዊ ፍርድ ሊወሰን የቻለዉ፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከአምስት መቶ በላይ ሙስሊሞች ከላይ በተጠቀሱት ወረዳዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የፍርድ ዉሳኔ የተሰጠዉም በተዘዋዋሪ ችሎት ነዉ፡፡ ዳኞቹም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡