Español

The title is "Le Bon Usage".

ትግራይ፤ ወጣት አልባ? ወይስ ሽማግሌ አልባ? (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

ለዚህ ጽሑፍ መነሻው ሃሳብ ክንፈ ዳኘው በአንድ ስብሰባ ቆሞ የተናገረው አስጸያፊ ንግግር ነው።

ጦርነቱ ትግራይን ወጣት አልባ አድርጓታል የሚባል ተደጋግሞ የሚሰማ ንግግር አለ። ትግራይ ግን ይበልጥ የተጎዳቸው በሽማግሌ እጦት ነው። ሽማግሌ ስንል ያረጀ፣ የሸበተ፣ እድሜው የተጎተተ ሰው ለማለት አይደለም።

ዛሬ በትግራይ እድሜ ጠገቦቹ ሰዎች የመለስ እኩዮች ናቸው። ሕወሃት በትነግ፣ በኢዲዮና በኢሕአፓ በደርግም ውስጥ የነበሩ የዚያን ዘመን የትግራይ ወጣቶችን እስከዘር ማንዘራቸው ደምስሳ ሕውሃታውያን ብቻ በሕይወት እንዲሰነብቱ ማድረጓ ይታወቃል። የሕወሃት መሪዎች ደግሞ ማገዱ እንጂ አልተማገዱም። በሃምሳ አመት ውስጥ በትግራይ በተደረጉት የማያባሩ ስብሰባዎች ኢትዮጵያዊነትን በቀጥታም ሆነ በገደምዳሜ ያንጸባረቁ ሁሉ በወረንጦ ተለቅመው ተወግደዋል። በቤታቸውም ተቀምጠው ከባንዳው ዓላማ በተቃራኒ የሆነ ነገር የተነፈሱም በአንድ ለአምስቱ ጥርነፋ እየተሰለሉ በሚስጥር ተወግደዋል።  ቤተክህነቱ ከዋልድባ፣ ደብረ ዓባይ፣ ደብረ ዳሞ ገዳማት ጀምሮ በሕወሃት ታጋዮች ተጥለቅልቆ ዛሬ ሕወሃቶች የትግራይ ተገንጣይ ሲኖዶስ ለማቋቋም እና የኢትዮጵያውንም ሲኖዶስ እንደብልና እንደነቀዝ በልተው ባዶ ለማድረግ ችለዋል።

እና መድረክ ላይ ሽማግሌ መስለው የሚቆሙት እነ ክንፈ ዳኘው፣ ተክለብርሃን (የቁጩ ጄኔራሎች) ወዘተ የሚያቀረሹት ከሽበታቸውና ከእድሚያቸው የሚጠበቅ፣ ትግራይን የሚመጥን ንግግር አለመሆኑ ሊያስደንቀን አይገባም። እድሜያቸው የገፋ አእምሯቸው እዚያው ጉርምስናው ላይ የቀረ የሕወሃት ማደጎዎች ናቸውና። እርጅና እንጂ ሽምግልና አያውቃቸውም።

የኮሌጅ ትምህርቱን አቋርጦ ሕወሃትን የተቀላቀለው ክንፈ ዳኘው ሕወሃት አዲስ አበባ ስትገባ የኮሎኔልነት ማእረግ ተችሮት የጂኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒካል ኢንስቲቱት ኃላፊ ከተደረገ ጀምሮ ሸዋን (እሱ እንደሚለው) ትርፍራፊውን ሳይሆን ዋናውን ቁርጥምጥም አድርጎ የበላ፣ በመጨረሻም የሕወሃት ጌቶች ተላላኪያቸው አቢይ አህመድን አዘው ወህኒ ያስወረወሩት ሰው ነው።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት በመንግሥት ለውጥ ወቅት አንድ የሚፈጽሙት የተለመደ ነውር አለ። እሱም አዲሱ መንግሥት ገና ሥልጣን ላይ እየወጣ ሳለ የሀገሪቱን ወታደራዊና የመሳሪያ ማምረት አቅም ዱቄት ማድረግ ነው። የሶርያ አማጺዎች በድል አድራጊነት ቤተመንግሥት ገብተው እየጨፈሩ ከጀርባ አሜሪካ እንግሊዝና እስራኤል የሶርያን የመከላከያ ተቋማት ቦምብ ሲያደርጉ እንደነበር የዘንድሮ ትዝታ ነው።  እኛም ጋር ደርግን እንደጣሉ ወያኔ የኢትዮጵያን የመከላከያ ሠራዊት እንድትበትን፣ የመሳሪያ ክምችት እንድታወድም ከማድረግ አልፈው፣ ወያኔን በበቂ ስላላመኗት ከሕንድ ውቅያኖስ በተተኮሰ ክሩዝ ሚሳይል የበቅሎ ቤቱን የመሣሪያ ዲፖ እስከማቃጠል ደርሰዋል (የፍሥሐ ደስታን መጽሐፍ ያነቧል)። የአየር ኃይልና የባሕር ኃይል አባላትንም ስደትና ፍልሰት በማቀላጠፍ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበትን የጦር ኃይል ባዶ አድርገዋል።

የቄሮን ለውጥ ተከትሎ፣ ክንፈ ዳኘውም ሜቴክ የሚባለው የመከላከያ የመሣሪያ ቴክኖሎጂ ማዳበሪያ ተቋም ኃላፊ ስለነበር ከሕወሃት ሌቦችና ወንጀለኞች ሁሉ እሱ ብቻ ተመርጦ እንዲወገድ እና ተቋሙ በአዲስ ተላላኪ እንዲመራ ተደርጓል። ማስተዋል የተሳነው ክንፈ ደግሞ ከሥራና ዝርፊያ ገበታው የነቀለውን የአልቆቹ አለቃ ዛሬም ባለማወቅ ለማገልገል “ትግራይ ሸዋና ኢትዮጵያን ተሸክማ መኖሯን አቁማ ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን የቀደመ ዓላማችንን እናስቀጥላለን” ይላል። የቀደመው ዓላማ የትግራውያን ሳይሆን የእንግሊዞችና የግብረ አበሮቻቸው መሆኑን በዚህ በአዛውንት እድሜው እንኳን ማስተዋል ያልቻለ የሸመገለ ሳይሆን የዛገ ሰው ነው።

በባንዶች ልጆች እጅ ከመውደቋ በፊት ትግራይ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ነበረች፣ ኢትዮጵያም (ሸዋም) ለትግራይ ባለውለታ ሆና ነው የኖረችው። ትግራይ በአክሱም አማካኝነት ለኢትዮጵያ የሃይማኖት (አይሁዳዊ፣ ክርስትያናዊ እና እስላማዊ) መሠረት ጥላለች፣ ሸዋም ትግራይ በባእዳን በተወረረች ቁጥር ኢትዮጵያን አስተባብሮ በመዝመት ነጻነቷን አጽንቷል። ከብዙ በጥቂቱ።

ሳይሸመግል የመዛጉ ምልክት ጣልያን ከዓድዋ በፊት በኤርትራና በትግራይ ያስቀጸለውን የሸዋ ጥላቻ ነው ዛሬም ክንፈ ዳኘው የሚያነበንበው። ጣልያን እኮ በሸዋ ላይ ያነጣጠረው የጥላቻ መርዙ እንዳልበጀው ስላወቀ ሸዋ፣ ሸዋ የሚለውን ትቶ አማራ፣ አማራ በሚል አዲስ የጥላቻ መዝሙር ነው ድኅረ ዓድዋ የተከሠተው።  ክንፈ ዳኘው ሕጻን ሆኖ ጡት ሲጠባ የሰማውን እንደያዘ ነው የጃጀው። ወይስ የጎንደርና የወሎን መሬት (ወልቃይትና ራያን) መርቁልን እና እንገንጠል ሲል ሸዋን አይከፋውም ብሎ ቆምሮ ይሆን?

ለማንኛውም ትግራይ የኢትዮጵያ ናት፤ ኢትዮጵያም የትግራይ ናት። ኢትዮጵያ ለትግራይ ብቻ የሆነ መሬት የላትም፣ የትግራይ ያልሆነ መሬትም የላትም። ዮዲትን ሸሽቶ ሸዋ የገባውም አክሱማዊ ነው፣ እዚያው የቀረውም አክሱማዊ ነው። አክሱም የአስክሱሞች የወላይታዎችም ነው። የመለስን የልጅነት ባንዳዊ ድንቁርና በእስተርጅና ማቀርሸት ለክንፈ እድሜ አይመጥንም።

ምንድነው? ወርቅ ወርቅ ሲባል ነበር፣ ከዚያም አልፎ ዳይመንድ፣ ነዳጅ ወይስ ታንታለም ተገኘ እንዴ? ፈረንጆቹ እንደሆነ ኮንጎ ሊያደርጉን እያንጃባቡን ነው። የማእድን ክምችት በያለበት አንዳንድ የጎበዝ አለቃ መንግሥት ሊያቋቁሙ። ዮክሬይንም አቧራው ሲዘቅጥ የማእድን ቁፋሮ ሆኖ ተገኘ አይደል የግርግሩ መዳረሻ? እግዚኦ!

ትግራይን “ሕየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ምትክ ልጆች ተወለዱልሽ) የምንልበትን ዘመን እንዲያመጣላት እንጸልይ እንጂ በአሮጌ ባንዶች ዲስኩር ሌላ ገደል እየተቆፈረላት ነው። እየተቆፈረልን ነው።

 

7 Comments

  1. This article should be a must read. I would like to appreciate the writer, my friend and brother in spirit, Ahungena Alemayehu for his concise and precise article which is full of bitter facts about our northerners, Tigrians. I read this piece now, and I have observed many similarities with that of my small piece posted this morning here on zehabesha.com. People speak the same language if they stick to reality, this is what I can say in the least.
    Though millions of Ethiopians are currently slumbering due to a number of reasons, please try to spread such realities mentioned here by Ahungena and let them make Ethiopians aware of what has been and being done by TPLFites to destroy ETHIOPIA. Thanks AA for your Jhonic cry in the desert. I hope people will come out of the den they are hidden now. And most of all, I would like to appreciate zehabesha.com as well for its resilience to serve Ethiopia while many others have detoured from the journey towards freedom.

  2. This article should be a must read. I would like to appreciate the writer, my friend and brother in spirit, Ahungena Alemayehu for his concise and precise article which is full of bitter facts about our northerners, Tigrians. I read this piece now, and I have observed many similarities with that of my small piece posted this morning here on zehabesha.com. People speak the same language if they stick to reality, this is what I can say in the least.
    Though millions of Ethiopians are currently slumbering due to a number of reasons, please try to spread such realities mentioned here by Ahungena and let them make Ethiopians aware of what has been and is still being done by TPLFites to destroy ETHIOPIA. Thanks A.A for your Jhonic cry in the desert. I hope people will come out of the den they are hiding now. And most of all, I would like to appreciate zehabesha.com as well for its resilience to serve Ethiopia while many others have detoured from the journey towards freedom.

    • አይ የኔ ነገር፤ ስቸኩል የምሳሳተው መብዛቱ – I wanted to mean Johnic, not Jhonic, I realized this spelling error when I was reading comments now. I know making such minute mistakes is not a big deal, but my sensitivity overrides me sometimes and hence I can’t help acting like this.

  3. ትግሬ ወጣትም ሽማግሌም አለው ግን ወጣቱን ከሽማግሌው መለየት ይከብዳል አሁን አቶ፤አባ፤አቡነ ሰረቀ ብርሃንን ድንጋይ ከሚወርውር ትግሬ በምን ትለየ(ያቸ)ዋለህ ቱግ ግንፍል ሲሉ የክርስቶስ ምልክት መስቀል እየወደቀ ጠያቂው ደንግጦ ሲያነሳው ብዙ ጊዜ ተመልክተናል። ለማንኛውም ጥልያን የነካው ሰው መቅኖ የለውም። አዲስ አበባ የከተሙት ባሱብን እኮ እነዛስ እሽ እዛው ናቸው። አሁን ደግሞ የተዘረፈው ብር እየሳሳ ሲሄድ እንደ ዘረፋም ነገር ያምራቸዋል ሱባን አላህ። ስሜነህ ቢፈርስ እንዳለው ያልሰረቁ ትግሬዎች ወሮ/አዜብ መስፍንና አቶ በረከት ስምኦን ናቸው እንዲህ ነው እንግዲህ የዘመኑ ጋዜጠኛ።

    • ጥሩ ፈገግ አደረከኝ ዙቡዳ። ጥሊያን የነካው ሰው መቅኖ የለውም። ጎሽ ልክ ብለሃል። አሰራራቸውም ከጣሊያን ፋሽሽት የተኮረጀ ነው። ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ (የባህል ጄኔራል) በመቀሌ ሲናገር ፌዴራል መንግስት መጋበዝ ማለት ውጫዊ ይዘት እንዲኖረው ያደርጋል እያለን ነው። ፈሪ፤ የድሃ ልጆችሽን አስጨራሽ ሌባ! ሴረኛው ወያኔን ከሞት ሌላ ወደ እውነት የሚያስጠጋው ምንም አይነት ምድራዊ መድሃኒት የለም። ቶሎ ቢጨራረሱ እንዴት መልካም ነበር። ግን ይጨርሳሉ፤ ያስጨርሳሉ እንጂ እነርሱን ሞት አይነካቸውም። ትጥቅ እንዲፈቱ ሲባል 100ሺህ ብር የሚቀበሉት የዛገና የማይሰራ የጦር መሳሪያ እያስረከቡ ነው። ግን ልበ ቢሱ ብልጽግና መሳሪያን መዝግቦ፤ ሲሪያል ቁጥራቸውን አመሳክሮ ነገሮችን መመልከት ጭራሽ አይችልም። የተጣለለትን መሳሪያ እንደ እንጨት ለቃሚ ታቅፎ ይጓዛል። ተንኮለኛው ወያኔ እንኳን ብልጽግናን ነጩን ዓለም ሳይቀር ማታለል የሚችል ከፍሎ ውሸት ማጻፍ፤ ከፍሎ ተቃዋሚን ማስገደል ኸረ ስንቱን የወያኔ ጉድ ብቻ የትግራይ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል፤ መሻሻል ይፈልጋል እያሉ እንሆ 50 ዓመት በባርነት ገዙ። እነዚህ ድርቡሾች በስልጣን ሲራኮቱ ማየትና መስማት ምንኛ ያማል። እንዴት ግን ስንቶቹን የሃገሪቱን ምርጥ ልጆች ሞት በጊዜውና ያለጊዜው ሲሟጥጥ እነዚህን እርኩሶች ዘለላቸው? አይ ፈጣሪ በእውነት በመንበርህ አለህ?

  4. እውነትም አለማየሁ ነብሰ ገዳይ ትግሬዎችን እየመረጥክ ነው በፎቶግራፉ ላይ ያሰጣሃቸው አረጋዊ በርሄም አላመለጠህም ብቻ ስብሃት ነጋ፤ በረከት ስሞን፤…አማረ የመሳሰሉት ተሰወሩብህ እንጅ። እነዚህ ሰዎች የቀን ጅብ ቢባሉ ምኑ ቅር ያሰኛቸዋል? በጠራራ ጸሃይ ጋቢ ይለብስ የነበረ ጎረቤቴ ቤቴ ደሳሳ ማድ ቤት ተከራይ የነበር ትግሬ ፎቅ በፎቅ ሲያደርጉት አውሮፓ በየሳምንቱ እየሄደ ኳስ መመልከት ጀመረ። የልጆቹ ነገርማ አይወራ ግምሹ ቻይና ግማሹ አውሮፓ ግማሹ አሜሪካ ናቸው ሁለመናው ሲለወጥ ያልለወጠው ስሙ ብቻ ነው አሁን አሁን አትጥሩኝ ገ/መድህን የክርስትና ስሜ ነው እያለን ነው። እስቲ የኦሮሞ ጥጋበኞችም ከዚህ ተማሩ የሃጢያት ስበት ሲጨምር አወዳደቅ ያከፋል ቤተ ልሄም ታፈሰ የተባለችውን ሴት ያየ ከተራበ ይልቅ ለጠገበ አዘንኩ ቢል ይፈረድበታል?

  5. ኡኡታው የማያልቀው ወያኔ ሲያለቅስና ሲያስለቅስ እድሜ ልኩን ኑሮ አሁን ላይ እርስ በእርስ መነካከስ ጀምሯል። ወያኔዎች የሚናገሩትና የሚያደርጉት ተግባር ጭራሽ ተገናኘቶ አያውቅም። የፕሪቶሪያ ስምምነት፤ ዲዲር ወዘተ እያለ አንድ የባህል ጄኔራሎች ሌላውን እየገፋ እንሆ ዛሬ ላይ ትግራይ ላይ የጦርነት ከበሮ ዳግመኛ እየደለቀ ይገኛል። ምዕራብ፤ ምስራቅ ትግራይ እያለ ህዝብ ያጭበረብራል። አልፎ ተፎም ሪፈረንደም በማለት ያላዝናል። ግን ይህ ሁሉ ለትግራይ ህዝብ ነው ይሉታል። የሰው አረመኔው ወያኔ እርስ በእርሱ የማይተማመን ለራሱ ብቻ የሚኖር ጥርቅም ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው በሸራተን ሆቴል የሰጠውን መግለጫ ላዳመጠ ነገርየው ሁሉ ተስፋ እንደሌለው ማስተዋል ይቻላል። ጌታቸው ዲዲሩን ያስቆመው የፌደራል መንግስቱ ነው ብዬ ለዓለም በውሽት ደብዳቤ ጽፌአለሁ። ግን ችግሩ የትግራይ የባህል ጄኔራሎች ባንዳ ብለው እንዳይጠሩኝ ያደረኩት እንጂ ፕሮሰሱን ያደናቀፍነው እኛው ነን ይለናል። ለ90 ደቂቃ ሲለፈልፍ አንድም ቁም ነገር ያለውን ነገር የለም። ይህ የሚያሳየው የትግራይ ህዝብ መከራ ገና ብዙ የሚያተራምስ ጉዳይ እንዳለ ነው። ለያዥ ለገራዥ ያስቸገረው ችግር ይላል ጌታቸው ይሄ ሁሉ የሚደረገው መንግስት በለቀቀው ባጀት የሚያምሱን ጄኔራሎች ናቸው ይላል። የፌዴራል መንግስቱም ዝም ማለትም ግራ የሚያጋባ ነው ይልና ግን የውጭ ሃይል ገብቶ ጦርነት እንዲቀጥል አንፈልግም ይላል። እነዚህ ሃሳባቸው የተጣረሰ የራሳቸውን ጥላ የማያምኑ የደም ሰዎች ለትግራይ ህዝብ ያኔም አሁንም አይጠቅሙም። በውጭ ሆኖ ለሚታዘብ የጌታቸው ሆነ የደብረጽዪን ቡድን ሁለቱም ለትግራይ ህዝብ አይበጅም። ውሸታቸው አንድ ነው። ትርምሳቸው ለስልጣንና ዘረፋ ብቻ ነው። የትግራይ በሽታ ወያኔ ባርነት ብቻ ነው። ባጭሩ ወያኔ እያለ የትግራይ ህዝብ ከመከራ አይወጣም። ፍትጊያው፤ ውሸቱ፤ ሌላውን መክሰሱ፤ ከሌላው በጦር መሳሪያ መዝረፉ፤ ወዘተ … ይቀጥላል። ወያኔ ማለት ሃርነት ሳይሆን ባርነት ነው። የጌታቸውም መንታ ሃሳብ አፈር ያነሳ ስጋ ነው። ምንም ቁም ነገር የለውም። ያኔም በሌላ ማላከክ አሁንም የውጭ ሃገራትን ድረሱልኝ ማለት ድሮም የሰማነው የጅሎች ጩኸት ነው። ችግሩ ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው። የትግራይ ወጣት ተነሳ እነዚህን ድኩማን ከጀርባህ ላይ አሽቀንጥር። ያኔ የትግራይ ሰላም ይመጣል። ይጸናል። ወያኔ እያለ ግን በጭራሽ ከጦርነት ውጭ ሌላ በጎ ነገር ለትግራይ ህዝብ አይሆንም። ሲኦል ድረስ ወርደን ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ያለው ጌታቸው አሁን ላይ ራሱ ቀድሞ እንዳይፈርስ ያስፈራል። ጌታቸውና መሰሎቹ እውነትን ተናግረው አያውቁም። የጌታቸውና የደብረጽዪን ፍትጊያ ለግል መኖር የሚደረግ መነታረክ ነው። ሌላው ሁሉ ፉርሽና የማታለያ ዘዴ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሕወሓት ዋነኛ ስኬት! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Next Story

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት [መኢአድ] የተሰጠ መግለጫ

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win