ስኬት ከተባለ የሕወሓት ትልቁ ስኬት ትግራይንና ትግሬዎችን ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መነጠል ወይም ማቆራረጥ ነው፡፡ ለዚህም ሥራው የኢትዮጵያ አምላክ አሣምሮ እየከፈለው ነው፤ ገና ወደፊትም አወራርዶ የማይጨርሰው የታሪክና የደም ዕዳ እየጠበቀው እንደሆነ ከግምት ባለፈ እርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ምድር እየሆነ ያለው አሳዛኝ ክስተት ሁሉ ለዚህ ግምት ዓይተኛ ምሥክር ነው፡፡ የዘሩትን ማጨድ ከአዳምና ሔዋን ጀምሮ የነበረና ያለ ነውና ይህን መሰሉ ሣቅና ልቅሶ ውርርስ እንግዳ አይደለም፡፡
አንድ ሕዝብ ከፋብሪካ እንደተመረተ ዕቃ – ፕሮ. መስፍን እንዳሉት – ማሰብና ማሰላሰል እንደማይችል ሁሉ በአንድ ጠባብ ቡድን ተወናብዶ ሀገርን ያህል ታላቅ ቅርስ ማጣት ከዕብደት የማይተናነስ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ጎጠኝነትና ሃይማኖት ሞኝነትን መሠረት እንደሚያደርጉ ከተጋሩ ይበልጥ መረዳት ይቻላል፡፡ መጽሐፉም ይናገረዋል፡፡ ዘረኝት ያሳውራል፤ ሃይማኖትም ካልተጠነቀቁበት/ለት እንደዚሁ ያሳውራል፤ ያሰክራል፤ ያሳብዳልም፡፡ ከሰሞነኛ ሀገራዊ ኹነቶች የምንረዳውም ይህንን ነው፡፡ አእምሯችን ሞቶ የተቀበረ እስኪመስል ድረስ ሁላችንም በየፊናችን ጠፍተናል፤ መንገድ ስተናል፡፡ ይህ በየፊታችን ተሸክመነው የምንዞረው ሆድ የሚባል ነገር ያላመጣብን የችግር ዓይነት የለም፡፡ እንኳንስ ከበስተኋላችን አልሆነ – ማንም አይተርፍም ነበር እስካሁን፡፡ ጎደል ባለ ቁጥር እየገፈተረ ገደል ነበር የሚከተን፡፡ የብርሃኑ ዘሪሁን ልቦለድ መጽሐፍም ይህን መስክሯል፡፡
ዛሬ በቲክቶክ ካየሁት ሰሞነኛ የተጋሩ ሰልፍ የተገነዘብኩት ከፍ ሲል የገለጽኩትን ነው፡፡ በሰልፉ የወያኔ ጥፍጥፍ የአልባንያ ይሁን የቻይና ኩርጅ ሰንደቅ ዓላማ ነው፡፡ አንድም ሰው የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም ሆነ ባላምባሻውን ወያኔ ሠራሽ የሰይጣን መታሰቢያ ባንዴራ አልያዘም፡፡ ለነገሩ መያዝ የሚሻ ቢኖርም በደቦ/በመንጋ መደብደብን ስለሚያስከትል ሊይዝ የሚደፍር አይኖርም፡፡ የምትገርም ትግራይ ተፈጥራለች፤ ኢትዮጵያም ገና ያልሞተችው አማሮችና ደቡቦች አካባቢ ነው፡፡ ይገርማ ወገኖቼ፡፡ በኔ ዕድሜ እንደዚህች ያለች ኢትዮጵያ ተፈጥራ አያለሁ ብዬ እንኳን በእውን በህልምም አላሰብኩም – በህልም ከታሰበ፡፡ አቢይን የመሰለ ሀገር-ጠል፤ ባዲራ-ጠል፣ ታሪክ-ጠል፣ ደም መጣጭና ዘረኛ መሪም ይመጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ እኔ እማውቀው “ከእንጨት መርጦ ለታቦት፤ ከሰው መርጦ ለሹት” የሚል ብሂል ነበር፡፡ የአሁኑ ሁሉም ነገር የዚህ ብሂል ተገላቢጦሽ ነው፡፡ ለማንኛውም የዚህ ሰውዬ ሥነ ተፈጥሮ ከምን እንደተሠራ ማትም ቋሚና ወራጁ፣ ምሰሶና ወጋግራው፣ ጣሪያና ግድግዳው ከምን ከምን ንጥረ ነገር እንደተበጀ ቢቻል በሕይወት እያለ ያ ባይቻል ሞቶም ቢሆን እንዲመረመርና እንዲታወቅ ማሳሰብ እፈልጋለሁ – በዚህ አጋጣሚ፡፡ ይህን ሰውበላ ሰው መሣይ ግለሰብ ማወቁ የወደፊት ታሪካችንን ለማረም ይጠቅመናልና ያልኩትን አስቡበት፡፡ በአሳቻና በአሳባሪ መንገድ ተሹለኩልኮ ቤተ መንግሥት በመግባት ለዳግመኛ ውድመት የሚዳርገን እንጭጭ ዜጋ እንዳይኖር የወደፊቱ ትውልድ በተለይ ከዚህ አስቀያሚ ታሪካችን ብዙ ሊማር ይገባዋል፡፡ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ እስኪያቅተን ድረስ መቸገር አይኖርብንም ለወደፊቱ፡፡ ግዴለሽነትና ምን ቸገረኝ ባይነት ደግሞ እያጠፉን ነው፡፡
ወደሰሜኑ ስመለስ ወያኔው ጌታቸው ረዳ ከጠበቅሁት እጅግ በወረደ ሁኔታ አንዱና ምናልባትም የመጨረሻው ደደብ ሰው ነው፡፡ አቢይን እንደማያውቀው አሁን ደርሶ ትግራይን ለማዳን ከጎኑ እንዲቆምለት ይማጸናል– አቢይ ጦም አያውቅም እንጂ ዳሩ “ማንን ብሎ ኩዳዴን ፆመ”ና ነው ጌቾ የርሱን እገዛ መጠየቁ? በአቢይ አገላለጽ ጅላንፎ ማለት እሱ ነው፡፡ አቢይ ትግሬንና አማራን እርስ በርስ ከውስጥም ከውጭም ማለትም ትግሬን ከትግሬ፣ አማራን ከአማራና ትግሬን ከአማራ አባልቶ ሥልጣኑን ለማጽናትና አክራሪ ኦሮሞዎች የሚቃዡባትን የኦሮምያ ኢምፓየር ለመመሥረት እንደሚፈልግ እየታወቀ የጌታቸው ተማጽኖ ድድብናን አጉልቶ ከማሣየት የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ በዚያ ላይ ከአቢይ ምንም ዓይነት አወንታዊ ነገር እንደማይጠበቅና ነገረ ሥራው ሁሉ ማለትም ተፈጥሮው እንዳለ በአፍራሽ ኃይል (Negative Energy) እንደተሞላ የማያውቅ የዓለማችን ዜጋ ቢኖር እርሱ ሞኝ ነው ወይም የለዬለት አስመሣይና አድርባይ ነው፡፡ አቢይ ማለት በተንኮል ክፋቱ ሣጥናኤል አብዝቶ የሚቀናበት ልዩ ብዔል ዘቡል ነው፡፡ በሥልጣኑ የመጡበት ከመሰለው በተለይ ልጆቹንም አይምርም እንኳንስ ሚስቶቹን፡፡ ይህን ሰው አለማወቅ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ለመረዳት የመጣበትን መንገድ (track record) ማየት ብቻ በቂ ነው – የገደላቸውና ያስገደላቸው ንጹሓን ዜጎች በስንትና ስንት truck ተጭነው ወደመቃብራቸው እንደተጓዙ ለማወቅም ጭምር፡፡ ስለዚህ ጌችዬ ያኔ በጦርነቱ ማብቂያ ገደማ ትግራይ ውስጥ አንድ አሮጌ ታዛ ሥር ተቀምጦ አቢይን በደምብ እንደሚያውቀው የተናገረውን ረስቶ እስከዚህ መዝቀጡ የሰዎችን ድርጊት እንጅ ንግግራቸውን እንዳናምን ለብዙኛ ጊዜ ያስታውሰናል፡፡
ወይ ኢትዮጵያ! አሁንስ መጨረሻዋ ናፈቀኝ፡፡ አብሮ በሠላምና በፍቅር መኖር ሲቻል በዘረኝነት መርዝ ተለክፎ በጥላቻ የገማ ጭቃ ተለውሶ እንዲህ መጠፋፋት ማንን እንደሚጠቅም ይህን የጨለማ ዘመን የሚሻገር ዕድለኛ ዜጋ የሚመሰክረው ይሆናል፡፡ መልካም መጋቢት 4/2017፡፡ መጋቢት … መጋቢት …. ለካንስ ይህ ወር አቢይን ያመጣብን መጥፎ ወር ነው፡፡