እምዬ ምኒልክ፤ የጥቁር ህዝቦች ኩራት

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የካቲት 23 ቀን፣ 1888 ዓ.ም የዛሬ 129 ዓመት ፤ የተደራጀ ኃይል ያለውን ፣ የኢጣሊያንን  ሠራዊት ፣ የእናት አገሩ መደፈር አንገብግቦት የምኒሊክን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ፣ በአብዛኛው  በትርና ጎራዴ ታጥቆ ፣ ከመላው ኢትዮጵያ ተሞ የመጣው  የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት በታላቅ ተጋድሎ አደዋ ላይ አሸንፎታል ።

በዚህ ድል ምኒልክ እና ጣይቱ በመሪነት የሚጠቀሱ ዋንኞቹ መሪዎች  ነበሩ ። መሪዎች በአንድ አገር በጎና መጥፎ ታሪክ  ውስጥ  ያላቸው  ሚና  ቀላል  አይደለም ።

የአገራችንን የኢትዮጵያ ታላላቅ መሪዎችን መቅደላ ፣ ጉንደት ፣ ጉራዕ ፣ ዶጋሊ ፣ መተማ ፣ አደዋ ፣ ኡጋዴን ፣ ኤርትራ ላይ ያላቸውን ታላቅ አበርክቶ ታሪክ  ያስታውሰናል ።

የቀደሙትን አባቶቻችንን የዘመናት ተጋድሎ ለታሪክ ትተን ፤ አፄ  ቴዎድሮስ ፣ አፄ  ዮሐንስ ፣ ዓፄ ምኒልክ አፄ  ኃይለሥላሤ ፣ ጓድ መንግስቱ  በመሯት ኢትዮጵያ እንኳ ባለ አገሩ ዜጋ በዘውግ ሳይከፋፈል በአንድነት እና በፍቅር ተሳስሮ ፣ ለአገሩ  ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ሚስቱን፣ ልጁን ፣ እናቱን ፣ አባቱን ፣ ወንድሙን ፣ እህቱን እና ዘመድ አዝማዱን  ከውርደት ፣ ከባርነት እና ከአሰቃቂ ሞት   አድኖል ። እነዚሁንም በመንበረ   የአገሩን ዳር ድንበር በደሙ አስከብሯል ።  ምንም እንኳን ከአደዋ ድልም በኋላ ፣ “ባህረ ነጋሽን  ” ኤርትራ ” በማለት ጣሊያን ቢያስተዳድራትም  ቅሉ  ።

” ባህረ ነጋሽን ” የዛሬዋን ” ኤርትራ ”  እስከ 1876  ዓ/ም ጀግናው ኢትዮጵያዊ  ራሥ አሉላ አባ ነጋ ያስተዳድሯት እንደነበር ይታወቃል ።  የያኔዋን ” ባህረ ነጋሽ ” የዛሬዋን “ኤርትራን ” አቶ መለሥ በወርቅ ሣህን ላይ በማድረግ  ለሥትራቴጂክ ጠላቶቻችን የዛሬ 33 ዓመት እንካችሁ በማለት  ፣ የሥልጣናቸው ማደላደያ ቢያደርጓትም ቅሉ  ።

( ይህንን ስጦታ አሜሪካኖች እንኳ በዲፕሎማሲ ቋንቋ ተቃውመውታል   ። ቢያንስ በደርድር አሰብን ኢትዮጵያ መያዝ ነበረባት በማለት  ። ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ  ለማልማት ከፍተኛ መዋለ ነዋይ ማፍሰሷ እና ከእርሷ ውጪ የወደብ ተጠቃሚ እንደሌለ ስለተገነዘቡ ነው  ፤ ኢትይጵያን ወደብ አልባ ማድረግ ለኤርትራም እንደማይበጅ የተናገሩት ። የኢሣያስ ለሽንፈት ና ለውድቀት የሚዳርግ ጫዎታ እና ስግብግብነት በወቅቱ እንዳልጣማቸው ኸርማን ኮሆን በገደምዳሜ ተናግረው ነበር ።  )

ኤርትራን ከእናቷ  ከኢትዮጵያ የመገንጠል ሤራ ፣ እጅግ የሚያንገበግብ ፣ ለአገር  ፍቅር መሞትን ከንቱ ና የከንቱ ከንቱ  የሚያደርግ ታላቅ የቅኝ ገዢዎቻችን ሤራ ነበር ።

( ዛሬም የኤርትራ መንገጠል የንገበግበናል ። ከብዙዎቻችን ልብ ውስጥ ቃጠሎው አልበረደም ። ለታላቋ  ሉአላዊት አገር ኢትዮጵያ የባህር በር ሲሉ ዘራይ ደረስ ና  አሉላ አባ ነጋ ከእስትራቴጂክ ጠላቶቻችን ጋር የሰሜኑንን ህዝብ አስተባብረው  በጀግንነት ተዋግተዋል ።  ጀግኖቾቹ አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰዋል ። ህይወታቸውን ሰጥተዋል ።  እነዚህን ኩሩ እና ጀግና ኢትዮጵያዊያንንም የማይረሳ አገር ተረካቢ ትውልድ አገራችን ዛሬም አገሬ አላጣችምና ነው ንዴቱና ቁጭቱ እየበረታ የመጣው  ።

በጥቅምና በብልጭልጭ ነገር የማይደለሉ ፣ አገራቸውን ከራሳቸው በፊት የሚያስቀድሙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም አሉ ።

ምዕሪብውያኑ ግን ዛሬም በጥቅም እየደለሉን  ፣ ሰውነታችንን  ዘንግተን ፣  ሟች መሆናችንን ክደን ፣ በጭፍን ጥላቻ እንድንገዳደል እያደረጉን ነው ።

በቁስ ሰቀቀን እና በሆድ ተገዝተን ፣ አፈር ለሚሆን ሰውነታችን እና ጥለነው ለምንሄደው  ቁስ የበለጠ ተጨናቂ አድርገውናል ።  ከአንድ መሐፀን የወጣ ወንድማችንን እንኳ እያስካዱን በጠላትነት እንድንተያይ አደርገውን በፀፀት ወደማቃብራችን ይሸኙናል    ።

ለህዝብና ለሀገር እንዳንጨነቅ በማድረግ አገራችንን እና ህዝባችንን በምፅዎት ኗሪ ሆነው እንዲኖሩ ለማድረግ ረቂቅ ሴራቸውን እየተገበሩ ያሉትን ምዕራብውያን አና  ሌሎችንም ትርፋቸውን ብቻ የሚያሰሉትን  ቱጃሮች  ይህ እሣት የሆነ ትውልድ ጠንቅቆ ያቃቸዋል ።

አደዋ ላይ እነዚህን አልጠግብ ባይ በዝባዥ ኃይሎችን ድል ለማድረግ መቻላችን ከነሱ ያላነሰ እንደውም የሚበልጥ አእምሮ እና ልብ እንዳለን የተገነዘብንበት ወቅት እንደነበር ያስታውሳልና   ።

በዛው ሞራል እንዳንቀጥል ግን በከፋፍለህ ግዛ መንገድ ፣ እንዴት በቋንቋ እንደለያዩን ፣  ከ1928  እስከ 1933 ፣ የአምስቱን ዓመት የተጋድሎ ዘመን  ሤራቸውን በመመርመር መረዳትም ችሏል ።

ይኽንን እውነት እነ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ፍንትው አርገው በግለ  ታሪክ መፀሐፋቸው ፅፈውት አንብቧልና ።

( አንድ ሰው በቋንቋ ልዩነት ብቻ እንዲጠላ የማድረግ ሥነ ልቡና በተደራጀ መልኩ በዜጎች ልብ እንዲሰርፅ የተደረገው በአምሥቱ ዓመት የኢጣሊያን ወረራ ጊዜ ነበር ።  መለሥም ” የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው ? ” ሲል ይኼ ስነ ልቡና ተጠናውቶት ነው ። ይኸ አፍረሽ ስነልቡና ግን በቅኝ ገዢ አገሮች ውስጥ የለም ። በደቡብና ሰሜን አሜሪካም የለም ። በዛሬዋ ኢሲያ አህጉርም የለም ። ኧረ ከኢትዮጵያ በስተቀር ዛሬ በአፍሪካም የለም ። ሰው በቃ ሰው ነው ። ቋንቋ አይደለም ። ከክርስቶስ ልደት በፊት 2000 ዓመት አስቀድሞ  የነበረውን ዝርያ ከቶም ቆንቋ አይገደውም ነበረ  ።  ከ15 ሺ ዓመት አስቀድሞ የነበረው ደግሞ  በምን ቆንቋ እንደሚግባባ አይታወቅም ነበር   ። (ሁሌም አዲስ ለሆነ ሆድ  ፣ ምቾትና ድሎት በማሰብ  ብቻ  የተፈጥሮን አመጣጥ መካድና የታሪክን እውነት  በውሸት መተካት ከንቱ ተግባር ነው ።  የራስን ትርክት ጎልቶ እንዲወጣ በማድረግ ዘላለማዊ ላልሆነ ምቾት ና ድሎት ሲባል የሚተገበር  ከንቱነት ደግሞ በታሪክ ሁሌም የሚያሶቅስ ይሆናል  ።    )

ታሪክ ለሥመ ጥር እና አርቆ አሳቢ መሪዎች ፣ የሰጠው ክብር በዚህ ትውልድ እንደገና ሊታደስ ይገባዋል ።እኛ ኢትዮጵያዊያን በአደዋ ድል አማካኝነት የተጎናፀፍነው ድል ለአፍሪካ ነፃነትን ፣ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣትን አጎናፅፏል ። የጥቁር የበታችነት እና ያለማወቅ ሐሰተኛ የነጮች ትርክት  በኢትዮጵያዊያን የአደዋ ድል ነበር  የተገለጠው  ።

” ነጭ  ኃያልና ሁሌም ተመላኪ ነው ” ብለው የሚያምኑ ቅኝ ገዢውች ጥቁር ኃያልና የአምላክ መገለጫ ክንድ እንዳለው የተገነዘቡት በአደዋ ድል ነው ።

ወደ አድዋ ፣ በሦሥት አቅጣጫ እየገሰገሰ የመጣው ፣ በሦሥት ጀነራሎች  የተመራው የሠለጠነው የኢጣሊያ ጦር  የተሸነፈው  ያለአንዳች ስስት ፣  ደረቱን ለጥየት በሰጠው ጥቁር  ኢትዮጵያዊ መሆኑ የጥቁሮች ትንሣኤ ነበረ   ።

ይኽ ድል በዛን ወቅት የዓለምን ኃያላን ያስደገጠ ነበር ። በተቃራኒው መላውን ጥቁር ህዝብን ያስፈነደቀ ነበር ። መላው ጥቁር ህዝብ የፈነደቀው  የነጭ የበላይነት አደጋ ላይ በመቀልበሱ ነው ። ” ጥቁርም ነጭን መግዛት ፣ ማሸነፍ መማረክና ምህረት ማደረግ ይችላል ። ” በማለት በጥቁሮቹ  ኢትዮጵያዊያን ድል አማካኝነት ሥነ ልቡናው ታደሱ ለነፃነት መፋለም የጀመረው ከአደዋ ድል በኋላ ነው ።

ከድሉ በኋላ ፣ በጀነራል ባራቴሪ ፊት አውራሪነት የሚመራውን  ጦር  ያ  በአገር ፍቅር ስሜት ልቡ የነደደው የኢትዮጵያ ባለ አገር አደዋ ላይ ድል ሲያደርገው የኢጣሊያን ህዝብ ለሚንሊክ ታላቅ የጀግና ክብር ሰጥቶ ነበር ።

የኢጣሊያንን ንጉስ ልጅ  ( አልጋ ወራሹን ) በእንኮኮ በመሸከም ፣ ህዝቡ በአጀብ ከቦ ” ምኒልክ ለዘላለም ይኑር ! ” በል እያለ ፣ ቀኑንን ሙሉ በሮም አደባባይ  እንዲጮኽ  እንዳደረገ መላው ጥቁር ህዝብ  ሲሰማ ደግሞ ፣ ያንን ጥቁር ንጉሥ አፄ ምኒልክን በእጅጉ ወዶታል ።

3 Comments

  1. የበደላችን ብዛት የረቀቀ ሱብኤ ላይ ሊያስገባን ይገባል፡፡ የምንሊክ አገር የጎበና ዳጨ አገር በአብይ መሃመድ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ደጽዮን፤ጊታቸው ረዳ፤ጻድቃን፤ሰየ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ሌንጮ ለታ ላይ ይውደቅ? አክሊሉ ሀ/ወልድ/ከተማ ይፍሩ እንኳንም ይህን ሳትሰሙ ሞታችሁ፡፡ እዛ አካባቢ ክብር ጠፍቶ ቅጥፈት ብቻ ሁኗል፡፡

  2. የበደላችን ብዛት የረቀቀ ሱብኤ ላይ ሊያስገባን ይገባል፡፡ የምንሊክ አገር የጎበና ዳጨ አገር በአብይ መሃመድ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ደጽዮን፤ጊታቸው ረዳ፤ጻድቃን፤ሰየ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ሌንጮ ለታ ላይ ይውደቅ? አክሊሉ ሀ/ወልድ/ከተማ ይፍሩ እንኳንም ይህን ሳትሰሙ ሞታችሁ፡፡ እዛ አካባቢ ክብር ጠፍቶ ቅጥፈት ብቻ ሁኗል፡፡

  3. የሚገርም ነው ጥልያን አገር የንጉሱን ልጅ “ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር” እያሉ ሲያሞግሱ ነጻ የወጡት ትግሬዎች የምንሊክን ስም አንስማ ይላሉ፡፡ ዶር መራራ እንዳሉት በብስኩት ያደጉ የሚሲዮን ልጆችም እንዴት የጥልያን ግብሩ ይዋረዳል ብለው ስለ አድዋ ድል አንስማ ብለዋል፡፡ መላው አለም ደግሞ በተለያየ መልኩ ያከብረዋል ግራ የገባ ነገር፡፡ የተምበረከኩበትና ቃታ የሳቡበት የሰውነታቸው ክፍል ቢተውላቸው ትንሽ ይሻላቸው ይሆን? የራያው ጌታቸው ረዳ ምኔ ተነካ ብሎ ነው መከልከሉ? አድዋና ምንሊክ ለዘላለም ይኑሩ ውለታችን እንዲህ ከሆነ ምን ይደረጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢብራሂም ትራኦሬ ቡርኪናፋሶ – የአቢይ አህመድ ኢትዮጵያ

Next Story

በአድዋ መንፈስ ተነሳስተን በአብይ አህመድ የሚመራውን የዘረኛ መንግስት እናስወግድ – አቶ መርሻ ዮሴፍና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

Go toTop