ጣምራ ፌደራሊዝም ወደ ፍጹም ኅብረት! – ገለታው ዘለቀ

September 8, 2023

በዓለም ላይ ሃገር የሚባለውን ግዙፍ ማህበር የመሰረቱ የሰው ልጆች ሁሉ ይህንን ማህበራቸውን ፍጹም የማይከፋፈል ማህበር አድርገው ና ይህንን ጠገግ የማይነካ ና የማይገሰስ አድርገው ይኖራሉ ። “ የማንከፋል አንድ ነን ….” “ህብረታችን ፍጹም ነው ….” ይላሉ። ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ደግሞ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የፈጠሩት ህብረት ፍጹማዊነት ይጎድለዋል። የሃገራችን ከፍተኛ ሰነድ የሆነው ህገ መንግስታችን ህብረታችን ፍጹማዊ እንዳልሆነ በጥብቅ ይገልጻል። ህብረታችን በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ የሚችል እንደሆነ ያሳያል። ኢፍጹማዊ የሆነ ህብረት ውስጥ ናት ሃገራችን። አስደማሚው ነገር ኢትዮጵያ በፍጹም ህብረት ውስጥ አለመግባቷና በየትኛውም ጊዜ ፈራሽ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ይ ህንን ኢፍጹማዊ ህብረታችንን የዴሞክ ራሲዎች ሁሉ ጥግ አድርገን መረዳታችን ነው የችግሮቻችን ሁሉ መሰረት። ይህ ገዢ መተሳሰሪያ መርሆ ወደ ታች በፖሊሲና በኑሮ ሲገለጽ ብዙ ግጭትና መፈናቀል አምራች ሆኖብን አይተነዋል። ስለሆነም ኢትዮጵያ ለውጥ ያስፈልጋታል። ታዲያ እንግዲህ ለውጥ ስንል ተፈላጊውን ለውጥ ማጥናት ኣለብን። እንዴት ነው ወደ ፍጹም ህብረት የምንሄደው ? እንዴት ነው በፍጹም ህብረታችን ውስጥ ብዝሃነት የሚስተናገደው ? እንዴት ነው አምባገነናዊ ባህርያትን የምንቋቋመው ? የሚሉትን ጉዳዮች ማጥናትና ከለውጥ ባሻገር ኢትዮጵያ የምትገባበትን የለውጥ ቤት ቀድሞ መስራት ያስፈልጋል። ይህ መጽ ሐ ፍ ያለው ፍላጎት ይሄ ነው። ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ እንድትሻገር ዋና ዋና መተሳሰሪያ መርሆዎቻችንን በሚመለከት ፍኖተ ካርታ ያቀርባል። —

መጽሐፉን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

 https://drive.google.com/file/d/1SDlnZaV7b8UFKjxO71oKZKNXkQ1S5rcV/view?usp=drive_link

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዳንኤል ክብረት ጎቤልሳዊ ፍፃሜ

ፋኖ
Next Story

የሀገርን ትንሣኤ ለማፋጠን ፋኖን ከሠርጎ ገቦች ሤራ መጠበቅ – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Go toTop