የአማራ ህዝብ ትግል ህልውናው የማረጋገጥ ተጋድሎ እንጅ የበላይ ሆኖ አዛዥ ናዛዥ የመሆን ፍላጎት አይደለም። የአማራ ህዝብ ትግል ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ መስፈን የሚደረግ ትግል ነው።
የአማራን ህዝብ ትጥቅ የማስፈታት እና ልዩ ኃይሉን የመበተን እና ፋኖን ለመደምሰስ የሚደረገው እንቅስቃሴ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ለመፈጸም የሚደረግ እንቅስቃሴ ዋና አካል ነው።
ይህም በመሆኑ መላው የአማራ ህዝብ ህልውናውን ለማረጋገጥ በክልሉ ውስጥ ምንም ዓይነት የመከላከያ ሠራዊት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ህልውናውን ለማስጠበቅ ተጋድሎ ማድረግ ይጠበቅበታል።
የአማራ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችለውን መዋቅር በመዘርጋት የአማራ ህዝባዊ ከሚቴዎችን በዋና ዋና ከተሞችና በወረዳዎች ማቋቋም አለበት።
ህዝባችን የተቋቋሙ መዋቅሮችን በመደገፍና በማጠናከር በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ውሰጥ አንድ አማራ አቀፍ ሸንጎ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ጥረት እንዲያግዝ ከጊዜያዊ ኮሚቴው ተወስኗል።
አሁናዊ የሕዝባችን ችግር በልኩ የሚረዱና ፈተናውን የማሻገር አቅሙ ካላቸው የሕዝቡ አብራኮች የተቋቋመው አመራ አቀፍ ሸንጎ መንግስት እንደሌለ አምኖ ሕዝቡን ከመምራቱ በተጨማሪ ከሕዝባዊ ኮሚቴው የሚሰጡትን የየዕለቱን የትግሉን ተግባራት ያከናውናል ከዚሁ አቢይ ኮሚቴ የሚሰጠውን የትግሉን መዳረሻ ለማሕበረሰቡ ያሰርጻል፣ ከጠላትም ሆነ ከኛው ባንዳዎች የሚነዙትን የሀሰት ወሬዎች ይገራል፣ በትግሉ ዙሪያ ያሉትን ብዥታዎች ያጠራል። በተጨማሪም ከየአካባቢው እየተፈናቀለ የሚመጣን የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ተቀብሎ ማስተናገድ እና የትግሉ አካል እንዲሆን መስራት ፋታ የማይሰጥ ተግባሩ ይሆናል።
በመሆኑም በዋና ዋና ከተሞች የምትገኙ ወጣቶች እና መላው የአማራ ህዝብ እየተዘረጋ ካለው አማራ አቀፍ ሸንጎ ጋር በመሆን የቤት ለቤት እንቅስቃሴ በማድረግ ከባለ ሀብቱም ሆነ ከአካባቢው ማህበረሰብ ሀብት በማሰባሰብ ስንቅ እና ትጥቅ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
ትግላችን እስከ ቀራኒዮ ነው። የትግላችን መዳራሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ።
የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ
ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም
ህልውናችን በክንዳችን