አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ

April 4, 2023
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት በገዢው ፓርቲ ተላልፏል ያለውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ። ውሳኔው፤ የአማራ ህዝብን “ያለ ተከላካይ ለዳግም ወረራ እና ጥቃት የሚዳርግ ነው” ሲል ፓርቲው ነቅፏል።
አብን በጉዳዩ ላይ ያለውን ተቃውሞውን ያስታወቀው፤ ወቅታዊ ጉዳይን በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 26፤ 2015 ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። ፓርቲው በዚሁ መግለጫው፤ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት ያህል አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደው የአብን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከተወያየባቸው “አንኳር ጉዳዮች” መካከል አንዱ የልዩ ኃይል ትጥቅ ማስፈታትን የተመለከተው አንዱ እንደሆነ ገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የታፈነው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ ኢትዮጵያዊ ቅንነትና ትልቅ ሙያዊ አቅም ነው !

Next Story

የአብይ አህመድ ኦሮሞማ መንግስት አፈና – የሃሰት ውንጀላ

Go toTop