የአብይ አህመድ ኦሮሞማ መንግስት አፈና – የሃሰት ውንጀላ

April 4, 2023

በመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጥቃት በመፈጸም ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሐይል አስታወቀ

በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በአዳማና በድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃቶች በመፈጸም ሀገራዊ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረሐይል አስታወቀ፡፡
የጋራ ግብረ ሐይሉ ለመገናኛ ብዙኅን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአማራና በሌሎች ክልሎች ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ እንዲሁም አዲስ አበባ ጭምር የሚገኙ ምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶችን ያካተተ ህቡዕ መዋቅር በምስጢር ሲንቀሳቀስ እንደነበር ተደርሶበታል።
ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን፣ ዶ/ር መሰረት፣ ወርቁ ተስፋዬ ወ/ማርያም፣ ተስፋዬ የኋላሸት ፋሲል፣ ሰለሞን ልመንህ ከተማና መንበረ የተባሉ ግለሠቦችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ሲሳተፉና ሲያስተባብሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

addisadmassnew

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ

ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቼው በምሽት 4:00 ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ተወስዷል። እስካሁን ያለበት ስፍራ አልታወቀም!
Next Story

የአማራ ሕዝብ ከዘረኛው አገዛዝ ጥቃት ለመዳን ፕላን ቢ አለው?

Go toTop