አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ እና ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አብርሃም ጌጡ ከጀርመን መንግሥት የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ከሆኑት ከቫንሳ ፕሪንዝ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጧል።
ውይይቱ የተደረገው መጋቢት 5/2015 ዓ/ም ሲሆን በውይይቱም በርካታ ጉዳዮች የተነሱ መሆኑ ታውቋል።
ከተነሱ ጉዳዮች መካከልም:_
1) በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለው ህገ ወጥ ቤት ፈረሳ፣
2) ወደ አዲስ አበባ የምግብ አቅርቦት አለመግባት፣
3) በሰላም ጉዳይ፣
4) በሀገሪቱ ወቅታዊ አጠቃላይ ጉዳይ፣
5) በሀገሪቱ ስለተከሰተው ጦርነት እና ውጤቱ፣
6) ሥለተፈፀመው እና እየተፈፀመ ሥላለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ፣
7) ስለተፈናቀለው ዜጋ እና በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ቤት ፈረሳን በተመለከተ፣
ግድያ፣ እስራት እና ንብረት ዘረፋ እንዲሁም አፍኖ መሠወርን በተመለከተ፣
9) በሀገሪቱ ውስጥ የደረሰው ድርቅ እና ረሀብ_በሰዎችና በእንሰሳት ላይ እያደረሰ ያለው ሞትና ሰደት፣
10) በአዲስ አበባ እየደረሰ ያለው የኑሮ ውድነት፣
11) ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸው በተለይም በአማራው ህዝብ ላይ ተጠናክሮ በቀጠለው ሰብአዊ የመብት ጥሠት ግልፅ በመሆነ መልኩ እየተፈፀመ በሚገኘው የዘር ፍጅት (genocide)
12) በሲዳማ እና ኦሮሞ ብሄረሠቦች እያንዣበበ ያለው ግጭት፣
13) በሶማሌ እና አፋር ያለውን የግጭት ሁኔታን በተመለከተ፣
14) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ያንዣበበው ግጭት፣
15) ህገ መንግሥቱን ተከቶሎ በተነሣ የክልልነት ጥያቄ የደቡብ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ፣ እስራትና ማዋከብ በተለይም በጉራጌና ወላይታ ላይ የሚደርሰውን እሥራት እና ግድያ፣
16) በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉዳይ፣
17) በፍትህና የህግ የበላይነት ጉዳይ፣
18) በግፍ በታሰሩት የመኢአድ ከፍተኛ አመራር – በሆኑት የእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ መምህር ዘመነ ጌጤ ቦጋለ እና
የአዲስ አበባ የመኢአድ ም/ቤት አባል እና የቀድሞው የአዲስ አበባ የመኢአድ ሰብሣቢ አቶ ቴዎድሮስ ማሞ እንዲሁም
የፓርቲው አባል የሆኑት አቶ አካሉ ተምትሜ በግፍ የታሰሩ መሆናቸውን፣
19) 17 በሚሆኑ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ሴት ተማሪዎችን ደብዛ ጠፍቶ መቅረትን በተመለከተ፣
20) በአዲስ በተካለለው የኦሮሚያ የአስተዳደር – ከተሞች ጉዳይ እየደረሰ ያለው ተቃውሞ፣
21) በጉጅ ፣ በነገሌ ቦረና ኦሮሞዎች ላይ የሚደርሰውን እስራትና ድብደባ በተመለከተ
ከ3 ሰዓት በላይ የወሰደ ውይይት እና ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።