ሰውየው ለሚመራው ህዝብ አክብሮት የሌለው ከአፉ በቀር በጭራሽ ሰብአዊነት የሌለው አደገኛ ህልመኛ ሰው ነው

December 9, 2022

የዜጎችን ደህናነት እና ሰላም ለማስጠበቅ ከፍ ያለ የገንዘብ ወጭ ይጠይቃል:: የገንዘቡ ወጭም: ሙያ ያለው የፓሊስ ሰራዊትን ለመቅጠር: የስለላ ስራን ለማካሄድ: ለግጭት ምክንያት የሆነውን የሃብት እጥረት ለማሟላት: በግጭቱ አካባቢ የተነቃቃ ኢኮኖሚ ለመፍጥሪያነት… ለመሳሰሉት ያገለግላል:: የእስከ አሁኑ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋው የአብይ አህመድ የቅንጡ ፕሮጀክቶች ወጭ ለዚህ አገልግሎት መዋል በቻለ ነበር:: ሰውየው ግን ከዚህ አስተሳሰብ በጭራሽ የራቀ ነው:: ከአፉ በቀር በጭራሽ ሰብአዊነት የሌለው: ከገሃዱ እውነታ ውጭ በራሱ ዓለም የሚኖር: የተንደላቀቀን ኑሮ የሚያሳድድ: ለሚመራው ህዝብ አክብሮት የሌለው: ህልመኛ ሰው መሆኑን በተደጋጋሚ በዜጎች ስቃይ በመቀለድ አስመስክሯል:: ብዙዎች ያልተረዱት: ይህ ሰው የሰው ስቃይ እና መከራ ጥቂት እንኳ ስሜቱን የማይቆረቁሩት: አሳሳች ሳዲስት መሆኑን ነው:: ኢትዮጵያ በዚህ ሰው እጅ መውደቋ እጅግ ያስቆጫል::

ሣሙኤል ገዛኸኝ በላቸው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የስነግጥም ቅርጽና ይዘት – Bedilu Wakjira Official Channel

Next Story

የፋኖ አንድነት ም/ቤት ተመሰረተ | ጥብቅ መልዕክት! | “ወልቃይትና ራያ ቀይ መስመሮቻችን”

Go toTop