ጋዜጠኛ ተመስገን በዋስትና የሚለቀቅ ከሆነ መከላከያ ሠራዊት “እርምጃ እወስድበታለሁ” ብሏል – ዐቃቢ ሕግ

July 20, 2022
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሐምሌ 18/2014 ጠዋት 3:00 ተቀጠረ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሠረ ጀምሮ በመንግስት ፍቃድ ያላቸውን (ቴሌቭዥንና ራዲዮ) መፅሔት፥ ጋዜጣ አና ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ እንዳያገኝ ተከልክሏል
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 14/2014ዓ.ም ጠዎት ልደታ 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቧል::
የዛሬው ቀጠሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የድርጀቱን ጉዳዮች በተመለከተ በአካል የግዴታ መገኘት እና መፈረም ለሚገባው ጉዳዪች ተመሰገን ከአንድም ሦስት ጊዜ በማመልከቻ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ቢያቀርብም ፖሊስ ይዤ አልሄድም የእጀባ አገልግሎትም አልሠጥም በማለቱ ነው ነበር::
ዛሬ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ወክለው ፍርድ ቤት የቀረቡት ዋና ሳጅን ፀጋው በዳሳ “አቃቤ ህግ መልስ ይስጥበት” የሚለውን መልሳቸውን በወረቀት አቅርበዋል::
ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉም “የአስተዳደራዊ ጉዳይ ስለሆነ አቃቤ ህግ ሳይሆን ፖሊስ ነው” የሚመለከተው ብለዋል:: ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ አያይዘውም “ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሰረበት ግንቦት 18/2014 ጀምሮ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ቴሌቭዥን፥ ራዲዮ፥ መፅሔት፥ ጋዜጣ አና ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ እያገኘ አይደለም በመሆኑም ደንበኛዬ ሀገሪቱ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ የማወቅ መብታቸውን ተነፍገዋል ሰለዚህ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይሄን መብታቸውን እንዲያከብር ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ይስጥልን” ብለዋለ::
ችሎቱም ለዚህ መልስ እንዳላቸው የጠየቀቸው ዋና ሳጅን ፀጋው በዳሳ “ከሚመለከተው ክፍል ጋር ተነጋግረን” እናሳውቃለን ብለዋል::
ችሎቱም በሁለቱም ጉዳዮች ላይ ውሳኔውን ለማሳወቅ ለሐምሌ 18/2014 ጠዋት 3:00 ቀጠሮ ሰጥቷል::
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስር ቤት ከሆነ ዛሬ ሃምሳ ስድስተኛ (56) ቀኑ ነው
ፍትህ_ለጋዜጠኛ_ተመስገን_ደሳለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአማራው ጩኸት (አንዱ ዓለም ተፈራ)

Next Story

አማራ እየታደነ በመጨፍጨፍ ላይ ያለው በአማራነቱ ነው፡፡ የሚድነውም በአማራነቱ ብቻ ነው!!

Go toTop