![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/07/DSCF7326-scaled.jpg)
በአንዳንድ ሀገራት ዋና ከተሞች የሀገሪቱ ርእሰ መዲና ይሆኑና ደግሞ የራሰ አስተዳደር መስርተው ይተዳደራሉ። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች አይጋጬም። አዲሰ አበባ የገባችበት አስተዳደር ግን ከዚህ አሰራር በጣም የተለየ በመሆኑ ከባድ መዋቅራዊ ግጭት ላይ ጥዷት ይገኛል።
ከመነሻው የብሄር ፌደራሊዝም ባለበት ሀገር ይህቺን ከተማ በልዮ ጥቅም እሳቤ እንድትጠየቅ ተደርጎ መዋቀሩ አንዱ የመጀመሪያው የአዲሰ አበባ የማሰናከያ ድንጋይ ነው። ይህንን ተከተሎ የሚመጣው የማህበራዊ ልዩ ጥቅም ፍላጎት፣ የኢኮኖሚ ልዩ ጥቅም ፍላጎት፣ የፖለቲካ ልዮ ጥቅም ፍላጎት አዲሰ አበባን የተከፋፈለች ከተማ (divided city) ለማድረግ በየቀኑ እየተጋ ነው። የከንቲባ አዳነች አመጣጥ ራሱ ከማንነት ጋር ተያይዞ የመጣ በልዩ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ሂሳብ የተደረገ ሹመት ነበረ። ይሄ አሳዛኝ ነገር ነው።
የአዲሰ አበባን ጥያቄ ለመፍታት መዋቅራዊ ችግሮቿን መረዳት ይገባል። የዛሬይቱን አዲሰ አበባን አስተዳደራዌ ቁመና ሰናይ ከተማዋን በሶሰት ፍላጎቶች (interest) ጉትቻ ከባድ ውጥረት ላይ ተጥዳ እናያለን። እነዚህ ሶሰት ፍላጎቶች
1. አዲስ አበባ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ይችላል የሚለው መሰረታዊ የአዲስ አበባ ህዝብ ፍላጎት፣
2. አዲሰ አበባ የፌደራል መቀመጫ ናት የሚለውና የፌደራል መንግስት ፍላጎት፣
3. የእሮሚያ ክልል ዋና ከተማየ ናት የሚዉ ፍላጎት ናቸው።
እነዚህ ፍላጎቶች ከማንነት ፖለቲካና ከብሄር ፌደራሊዝም ሸለቆ ውሰጥ መሽገው ይራኮታሉ። በዚህ ሳቢያ ከተማዋን መዋቅራዊ ግጭት ላይ ጥደዋታል። ይህ ከባድ ችግር መለወጥ አለበት። አዲሰ አበባን ከልዩ ጥቅም እሳቤ መንጋጋ በማላቀቅ የመዋቅር ግጭቶችን መፍታት ካልተቻለ የተከፋፈለች ከተማ አድርጎ መከራዋን ያራዝማል። አንድ ዋና ከተማ ከፍ ሲል ያነሳኋቸው ሶሰት አስተዳደራዊ ዝንባሌዎች የሚፋተጉበት መዋቅር ላይ ከወደቀ ይህ የመዋቅር ግጭት ከፍተኛ አለመግባባትና ትርምስን ያመጣል። ሰለዚህም ይህ ግጭት እልባት አግኝቶ ልዩ ጥቅም ቀርቶ በእኩልነት የምንተዳደርባት ከተማ እንድትሆን የመዋቅር ግጭቶች እንዲፈቱ ትግላችን ይቀጥላል።
በአንዲት የማትከፋፈል ኢትዮጵያ ስር የማትከፋፈል ጠንካራ አዲስ አበባን መገንባት ያሰፈልጋል።
እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ
ገለታው ዘለቀ