በቻይናውያን አፈ ታሪክ ውስጥ ጣዎስ (peacock) ጅራቱ ላይ ያሉት የሚያምሩ ቀለሞች እና “ዓይኖች” ዝናን (fame) እና መልካም እድልን ( good luck) ያመለክታሉ ተብሎ ይታመናል፡፡
ጣእስ በተለያዩ ባህሎችና ነገስታቶች ዘንድ በተለያዩ ትርጓሜዎች በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል በአብዛኛው ልዩ በሆነው ውበቱ ፣ ጥንካሬን ፣ በራስ መተማመንን እንዲሁም ከፈጣሪ የተሰጠ መለኮታዊ ኃይልን ( divine power ) ይወክላል ተብሎ ስለሚታሰብ በቀዳማውያን ነገስታቶች ተመራጭ ምልክት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይነግሩናል፡፡
እንደ ግሪኮች፣ ግብፃውያን እና ሮማውያን ባሉ ጥንታዊ ባህሎች ውስጥ የፒኮክ እይታ ከአማልክት ወይም ከሌሎች መለኮታዊ ፍጡራን የተሰጠ ስጦታ እንደሆነ ይታሰብ ነበር። ስለዚህ ጣኦሶች እንደ ዕድለኛ የችሮታ ምልክት ትልቅ ዋጋ ተሰጥቷቸው ኖሯል፡፡
በ 13 ኛው ክፍለ ዘመን ወረራ የፈፀሙት ሞንጎሊያውያን ይለብሱት ስለነበር በምስራቅ አውሮፓ የፒኮክ ላባዎች በተለምዶ የመጥፎ እድል ምልክት ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ በአንጻሩ ፒኮኮች የሕንድ ነገሥታት ንጉሣዊ ምልክቶችም ነበሩ። ጣኦሶች በአንዳንድ ሀገራት በጣኦትነት እስከመመለክ ደርሰዋል፡፡ ፒኮኮች ሞተው ስጋቸው አይፈርስም ተብሎ ስለሚታሰብ የህያውነትና የዘላለማዊነት ምልክትም ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡
ስለፒኮክ በርካታ ድርሳናት ሰፊ የሆነ ትንታኔና ታሪካዊ ትርክቶችን አስፍረው ያለፉ ሲሆን ለመነሻ ያህል ከላይ ያሉትን ካልኩ ዘንዳ ወደዋናው ነጥቤ እወስዳችኃለሁ፡፡
ጠ/ሚ አብይ አራት ኪሎ ምኒሊክ ቤተ-መንግስት እንደረገጠ ያደረገው ነገር ለዘመናት በቤተ-መንግስቱ በምልክትነት የተቀመጠውን የአንበሳ ሀውልት አፍርሶ በጣኦስ መተካት ነበር፡፡
ታዲያ! ጠ/ሚ አብይ ባለፉት አራት አመታት ከሚያሳየው ባህሪ ፣ ከተግባራቱና ከንግግሩ ተነስቼ ” ህወሓት እንኳ ያልደፈረውን ወይም ያልፈለገውን ቅርስ የማጥፋትና ምልክት የማሳጣት ተግባር አብይ በዚያ ፍጥነት እንዴት ሊያደርገው ቻለ? ” የሚለውን ጥያቄ ለመረዳት ሞክሬአለሁ፡፡
ከጣኦሶች ምልክታዊ መገለጫነት አኳይ ይህን የጠሚው የፒኮክን በምልክትነት የመጠቀም ሁኔታ ለመረዳት ስሞክር በመጀመሪያ ከፊቴ ድቅን ያለው << ..እኔ ከህፃንነቴ ጀምሮ 7ተኛው ንጉስ እንደምሆን አውቃለሁ! እናቴም ትንቢቷን ነግራኛለች!” የሚለው የመድረክ ድስኩሩ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ቁጡውና መልከመልካሙ ታኦስ ” ከፈጣሪ የተሰጠ መለኮታዊ ስልጣን እንዳለው በማሰቡ” የወሰደው እርምጃ መስሎ ይሰማኛል! የእናንተን በኮሜንት አጋሩኝ!
በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለፓርቲው በአርማነት ከተጠቀሙት ጀምሮ በምርጫ ምልክትነት እስካዋሉት ምልክቶች ብሎም በየፓርኩና በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ እንዲቀመጥ ያደረጓቸው ቅርፃቅርፆች ሁሉ በቀጥታ የሚከተሉት አምልኮ ውክልና ያላቸው ናቸው፡፡