አቢይ አህመድ በዛሬው የፓርላማ ውሎው የፖለቲካ አላዋቂነቱና ድንቁርናው ለይቶለት ፍጥጥ ብሎ በመውጣቱ ብዙዎች “የአእምሮ በሽተኛ” እያሉት ነው

July 7, 2022

ሀ. “አሜሪካ ውስጥ በስድስት ወራት ብቻ 20 ሺህ ሰዎች ሞተዋል ስለዚህ በኢትዮጵያ የሞተው ሰው ቁጥሩ ከዚህ ግባ አይባልም…” በማለት አድበስብሶ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ሰውየው ፒ.ኤች.ዲውን ያገኘው በጓሮ በር ነው የሚባለው እውነትነት አለው! በእርግጥ ያልተማረ ሰውም ይህን ከድንቁርና በታች የሆነ ሀሳብ ይናገረዋል ተብሎ ፈፅሞ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ አሜሪካ ውስጥ ሰዎች የሚገደሉበትንና ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ ነገድ ብቻ ተለይቶ የሚጨፈጨፍበትን አውድ እንተወውና ደንቆሮው አቢይ አህመድ በተነተነበት መንገድ ሞትን በቁጥር እናነፃፅር ብንል አሳዳጊዎቹ ወያኔዎችና እሱ ራሱ በቀሰቀሱት ጦርነት ብቻ ሚሊዮኖች ረግፈዋል፤ በወለጋ ምድር በየቀኑ የሚጨፈጨፈው ሰው እውነቱ ስለማይነገር እንጂ ቁጥሩ የትየለሌ ነው፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የሰዎች መታረጃ ቄራ ሆናለች፤ አገዳደሉን ራሱ ብናይ አሜሪካ ግፋ ቢል በጦር መሳሪያ እሩምታ ተኩስ ነው ሰዎች የሚገደሉት እዚህ ግን በተለይም ወለጋና ቤኒሻንጉል ሰዎች በዘግናኝ መልኩ በስለት ይታረዳሉ፤ በቀስት ይወጋሉ፤ ህጻናት በማጅራታቸው በሳንጃ ታርደው ስጋቸው እንደ ዶሮ ተበልቶ ለቀባሪ አስቸግሮ ይገኛል፤ እርጉዝ ሴቶች ሆዳቸው በሳንጃ እየተቀደደ ሽላቸውን በእጆቻቸው እንዲታቀፉ እየተደረገ ነው፤ የአራት ቀን፣ የአምስት ቀን አራሶች ጨቅላ ህፃናት ከእናቶቻቸው ጋር በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው፤ የሰው ስጋ ተበልቷ፤ ሰው ከእነ ነብሱ ተቃጥሏል… ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው እንግዲህ ዘር ጎሳና ነገድ እየተመረጠ ነው፡፡

ለ. “መንግስት በቅድሚያ የህዝቡን ሰላም ይጠብቅ” ተብሎ ሲጠየቅ ደግሞ “ህዝቡም የመረጠውን መንግስት እየሰማ አይደለም… ለሰላም አልቆመም…” በማለት ጥፋቱን ወደ ህዝብ ለማላከክ ሞክሯል፤ በእርግጥም ይህ አባባል በዓለም የሌለ ንግግር በመሆኑ አብዛኞቹ የአእምሮ ህመም አለበት ቢሉ የሚፈረድ አይደለም፤ “ህዝብ እየተጎዳ ስለሆነ መንግስት ለህዝቡ ይድረስለት” ተብሎ የተጠየቀ የአገር መሪ “ህዝቡ ራሱ ነው ጥፋተኛ” ብሎ ለማምለጥ ሲሞክር ስታይ ሰውየው አእምሮው ገና አልበሰለም በእንጭጭ ደረጃ ነው የሚገኝ፣ ግልብና ጥሬ ነው ብለህ የምታልፈው ብቻ አይደለም፤ ሆነ ብሎ አገር ለማፍረስ እየሰራ ነው ብለህም እንድታረጋግጥ ያስችልሃል፡፡ ብቻ ለዚህ ምገልፅባቸው ቃላት ስለሚያጥሩኝ ይህን ብቻ ብየ ልለፈው…

ሐ. የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የጠየቁትን ሲመልስ “እዚህ በመንደር ተደራጅታችሁ መጥታችሁ እኛን ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅት ይዘን የተቀመጥነውን፣ ለኢትዮጵያ አንድነት የምንለፋውን… አትውቀሱን…” ብሎ በድፍረት ተናገረ፡፡ ጠያቂው ሰው አባቱ ይሆናሉ፤ ምንም አይነት ክብር ሳይሰጣቸው ሊያበሻቅጣቸው ሞከረ፤ ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለአማራ ህዝብ ያደረበትን ንቀት ያሳያል፤ ምክንያቱም ሰውየው የአማራ ተወካይ ናቸውና፤ በሌላ በኩል ደግሞ እሱስ ገና ከአስራ አራት ዓመቱ ጀምሮ በመንደር የተደራጀው ህወሓትን ተቀላቅሎ እድሜውን የጨረሰው በኦህዴድ የጎሳ ፖለቲካ አይደለምን? አሁንስ ቢሆን የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማራ ብልፅግና፣ የደቡብ ብልፅግና፣ የሶማሌ ብልፅግና፣ የአፋር ብልፅግና፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና… ወዘተ በሚል የመንደር ፓርቲ እንጅ መቼ በተግባር አገራዊ ፓርቲ መስርተው ነው ጉራውን የሚነፋብን? መጀመሪያ ያወጡትን ማለትም ገና ይፋ ሳያወጡ በውስጥ የሰየሙትን “የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ” የሚል ስም ጥለው “ብልፅግና ፓርቲ” የሚል ስያሜ ይዘው ብቅ ያሉት እኮ የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማራ ብልፅግና፣ የደቡብ ብልጽግና… እያሉ በየመንደሩ ሸንሽኖ ለመጥራት እንዲመቻቸው ነው፤ በኢህአዴግና በብልፅግና መካከል የስም እንጂ የተግባር ለውጥ የለም፡፡ ብዙ በጣም ብዙ ማለት ይቻል ነበር ከዛሬው ንግግሩ ሃሳብ እየመዘዙ ግን ከንቱ ድካም ነው ሚሆነው፤ እንደዚህ አይነት ሃፍረትየለሽ ወራዳና ውሸታም ሰው በዓለም ላይ ታይቶ አይታወቅም…

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ነፃነትህ በእጅህ! (በላይነህ አባተ)

Next Story

እንኳን አገር ቤተሰብ መምራት አትችልም – የአቶ አብይ አህመድ የፓርላማ አሳዛኝና አስቂኝ ጥቅሶች

Go toTop