የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዛሬ የፓርላማ ውሎ

July 7, 2022

ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሲቪሎች ላይ የሚፈፀመው ግድያ በመንግሥት ቸልተኝነት የሚፈፀም እንደሆነ የሚቀርቡ ክሶችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተባብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሲሰጡ ለጥቃቶቹ ተጠያቂ ያደረጉት “ሸኔ” ብለው የጠሩትን ቡድን ነው። ቡድኑ “የፖለቲካዊ ዓላማ የሌለው የሽብር ተግባር በመፈፀም ላይ ያለ ነው” ሲሉ የወነጀሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “መንግሥት በቡድኑ ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚለው ቡድን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚፈፀሙትና ሰሞኑንም ለተፈፀሙትም ጥቃቶች ተጠያቂ ያደረጋቸው “በመንግሥት መዋቅር ውስጥ አሉ” ስለተባሉ ሰዎችም ተጠይቀው “መንግሥት በእነርሱ ላይም እርምጃ እየወሰደ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ፓርቲያቸው ከህወሓት ጋር ለመደራደር ስለደረሰበት ውሳኔም ተጠይቀው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/

VOA

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዋሽንግተን ሰልፍ ክብር ለተጨፈጨፉት!! የኢትዮዽያ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ተደርጎ ተውለውልቧል!

Next Story

ትላልቆች ታናናሾችን ያስተምሩ፣ ሁላችንም ለሕዝባዊ ውይይት እንነሳ!! – ከበየነ ከበደ

Go toTop