ኢዜማ እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል እና የተቋቋመበትን ዋነኛ አላማ እና ግብከማሳካት ይልቅ፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር በመለጠፍ መስመሩን መሳቱ እጅግ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ነው።
በመሆኑም ከዚህ በሗላ ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ የሚያስብና ለመታረመም ለመቃናትም ዝግጁ ያልሆነ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም።
እምነት ጥዬ የገባሁበት ፓርቲ አላማውን ስቶ ወደ ገባበት የቁልቁለት ጉዞ አብሬ ለመግባትና የታሪክ ተወቃሽ ለመሆን ህሌናዬ አይፈቅድልኝም። በመሆኑም ከኢዜማ አባልነቴ በፈቃዴ ለቅቂያለሁ።
(ክቡር ገና – የኢዜማ ከፍተኛ አመራርና ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የተወዳደረ ከመልቀቂያ ደብዳቤው ላይ የተወሰደ)