ጀነራል ተፈራ ማሞ ያሉበት ሁኔታ ደብዛ እንደጠፋ ቤተስቦቻቸው ትናገሩ

May 18, 2022
የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ ትናንት እረፋዱ ላይ ሰው ለማግኘት አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መውጣታቸውን የሚናገሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይለማሪያም፤ ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ቢደውሉም እንደማይነሳና ዛሬም ወደ ተለያዩ የፍትህ ተቋማት ቢሄዱም ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል።
“ትናንት ረፋዱ ላይ ከአቶ ዩሐንስ ቧያለው ጋር ቀጠሮ እንዳለውና እርሱን ለማግኘት እንደሚሄድ ነግሮኝ ነበር ከቤት የወጣሁት” ያሉት ወ/ሮ መነን “ሁሌ ስብሰባ ወይም ሌላ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ጉዳይ ሲኖረው ስልክ ደውሎ ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ያለበትን ሁኔታ ያሳውቅ ነበት ትናንት ግን ይህን አላደረገም። ሁኔታው አላምር ሲለኝ ስልኬን አንስቼ ደጋግሜ ደወልኩ ስልኩ አይነሳም አቶ ዩሐንስ ጋር ደወልኩ እስከ 10:30 ድረስ አብረው እንደነበሩና ወደ መኪናው አስገብቶት እንደተለያዩ ነገረኝ ማታም የቅርብ ዘመዶቻችን ጋር ስደዋውል አየሁት የሚል ሰው አላገኘሁም” ብለዋል።
ዛሬ ጠዋት ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሄዱም ሊያገኟቸው እንዳልቻሉና በኋላም ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ሲሄዱ በነገው ዕለት ወረቀት ፅፈው ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
VOA
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ

\

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እጮሃለሁ! – ብሩክ ነኝ

Next Story

ይድረስ ለኦሮሞ አባቶችና ልሂቃን – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Go toTop