![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/05/280178087_1167420260691020_2546484732689969147_n.jpg)
የቀድሞ የትግል አጋሬ ፣ የሥራ ባልደረባዬና ወዳጄ የነበረው ጓድ ኮ/ል ፍስሐ ደስታ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልፃለሁ ።
ጓድ ኮ/ል ፍስሐ ደስታ ከአብዮቱ ዘመን ዋዜማ ጀምሮ እስከ ኢሠፓአኮ / ኢሠፓ ምስረታና ኢህዲሪ መንግሥት መቋቋም ድረስ ሀገራችን እና ፓርቲያችን የሰጠውን ኃላፊነት በሙሉ ትጋትና ቁርጠኝነት የተወጣ ጓድ ነበር ።
ኮ/ል ፍስሐ በሚያቀርባቸው ሃሳቦች መንግስትና ፓርቲያችን በእጅጉ ተጠቃሚ ነበሩ ። ጓድ ፍስሐ ሀገሩን እና ህዝቡን ከልብ የሚወድ ፤ ከሌብነት የፀዳ ፤ ከብሔርና ጎሳ አስተሳሰብ ፍፁም ነፃ የሆነ ታማኝ የሕዝብ አገልጋይ ነበር ።
ለቤተሰቡ ፣ ለቀድሞ ባልደረቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ ልባዊ መፅናናትን እየተመኘሁ ለጓድ ኮ/ል ፍስሐ ደስታ ሰላማዊ እረፍትን እመኛለሁ።
ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም
የቀድሞ የኢህዲሪ ፕሬዚዳንት
ሚያዚያ 29 /2014 ዓ.ም
ዚምባብዌ /ሐራሬ
![©️](https://static.xx.fbcdn.net/images/emoji.php/v9/te8/1.5/16/a9.png)