የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛው ከአንድነት ጽ/ቤት ሲወጣ በመኪና ተገጨ

February 18, 2014

(ፍኖተ ነፃነት) ጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትና “ገና እንገድልሃለን” የሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው ጽ/ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ አድርሶበታል፡፡ “ገጭታቸሁኝ ወዴት ትሄዳለትሁ” በማለት ሲጠይቃቸውም “ገና እንገድልሃለን” ብለውት እንደሄዱ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡

ጋዜጠኛው ላይ የመኪና አደጋ ያደረሰው ታክሲ ውስጥ ሹፌሩና አንድ ግለሰብ ብቻ እንደነበሩም ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር በአሁኑ ሰአት ጉዳዩን ለፖሊስ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡

Previous Story

Hiber Radio: አንጋፋው የሜጫና ቱለማ አመራር ስንብትና ሕወሃት ሜጫና ቱለማን ለማዳከም የወሰዳቸው እርምጃዎች (ወቅታዊ ዘገባ)

Next Story

የአውሮፕላን ጠለፋውና የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ (አጭር ወግ)

Go toTop