ባንቺ ነው አድዋ – በነሲቡ ስብሐት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. የአድዋን ድል ምክንያት በማድረግ

February 27, 2022

 

 

ባንቺ ነው አድዋ” በነሲቡ ስብሐት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. የአድዋን ድል ምክንያት በማድረግ።

 

 

አድዋ
የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።
.
እጅጋየሁ ሽባባው ( ጂጂ) – አድዋ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ወልድያ ከተማ ሁለተኛውን ዙር ወታደራዊ ሰልጣኝ ተወርዋሪ እጩ ፋኖን ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም በማስመረቅ ላይ ነች። (ወልድያ ከተማ)

Next Story

ዐብይ አሕመድና የኦነግ አራጅ ሠራዊት – መስፍን አረጋ

Go toTop