የዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ፣ የአውሮጳ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች የሩሲያን አጥብቀው ኮንነዋል። መሪዎቹ ሩሲያ ጥብቅ ማዕቀብ ይጠብቃታል ሲሉ ተናግረዋል። የተመየስደተኞች መርጃ ድርጅት ሩሲያ በዩክሬን በጀመረችው ወታደራዊ ወረራ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያስከትለው ሰብዓዊ መዘዝ አስከፊ” እንደሚሆን አስጠነቀቀ። ዩክሬይን ወደ 40 የሚሆኑ ወታደሮቼ ተገድለዉብኛል እያለች ነዉ።
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ “በኮሚሽኑ አሰራር ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚኖር ከሆነ ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ” መናገራቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።
ሙሉዉን ዜና የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!