ከዛሬ ሶስት አመት ተኩል በፊት የተካሄደው የብአዴን/አዴፓ 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እንደ ድርጅታችን ስም ምግባርና ግብራችን እንቀይራለን ብለን አስበን፣ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ቆጥረን አንስተን፣ የጉባኤ ውሣኔ አድርገን፣ ለአማራ ህዝብ ተስፋ ሰጭ ፖለቲካዊ አቋም ይዘን ብቅ ብለን ነበር።
በድርጅታዊ ጉባኤው አቋም የተወሠደባቸው የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች፦
- የወልቃይትና የራያ የወሠንና የማንነት ጥያቄን እንዲፈታ ማድረግ
- ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን የአማራ ህዝብ መብቱ ተከብሮ በሠላም እንዲኖር፣ ተመጣጣኝ የሆነ የፖለቲካ ስልጣን ውክልና እንድኖረው ማድረግ
- በአማራ ህዝብ ላይ የተዘራው የጥላቻና የሀሠት ትርክትን እንዲለወጥ የሚያደርግ ስራ መስራት
- በሃገሪቱ ከሚካሄድ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ከአድሎ በፀዳና በግልፅ በሚታወቅ መርህና በሚዘጋጅ የህግ ማቀፍና የአሠራር ቀመር መሠረት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
- አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚባል የሽግግር ጊዜ ፖለቲካዊ ፕሮግራም በማንኛውም አግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል እንድደረግ
- ለአማራ ህዝብ ይሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ የችግሮች ሁሉ መነሻ የሆነው ህገ መንግስት እንዲሻሻል እንታገላለን ብለን የአቋም መግለጫ አውጥተን የጉባኤ ውሳኔ መሆኑ ግልፅ እውነታ ነበር።
ከእነዚህ የጉባኤ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱን እንኳን ሳንተገብር ለ13ኛው ወይም ለብልፅግና መስራች ጉባኤ ዝግጅት እየተደረገ ነው። የብልፅግና መስራች ጉባኤ ለአማራ ህዝብ ምን ይዞለት ይመጣ ይሆን? አብረን የምናዬው ይሆናል።
የአማራ ህዝብ አሁን ቢያንስ ቢያንስ በቋንቋውና በደሙ ምክንያት ሞትና መፈናቀል ሊቆምለት ይገባል !!