፹፭ ኛዉ ዝክረ አደዋ ድል ታሪክ ወይስ ንትርክ? – ማላጂ

February 21, 2022

የየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱ መቶ ፳፱ ዓ.ም. ገዳዩ እና ወራሪዉ የኢጣሊያ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ በደረሰ ፍጂት ሠማንያ አምስተኛ ዓመት ተከብሯል፡፡

በዚህም የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖርም ዕዉነቱ ግን የመላዉ ጥቁር ዘር የሖነዉ የሠዉ ልጆች የባርነት እና የሞት ቀንበር የተሰበረበት የአድዋ የትግል ፍሬ የሆነዉ የአድዋ ድል ነበር ፡፡

ይህም አስካሁን ካለዉ በላይ በኢትዮጵያዉን እና ኢትዮጵያ ምድር ብቻ ሳይሆን በመላዉ የሠዉ ልጆች ሊሆን በተገባ ነበር ፡፡

የአድዋ ድል ሲወሳ የኢትዮጵያዉያን የአልገዛም ባይነት የነፃነት ትግል ተጋድሎ መሆኑን እና አሁን ላይ እና ወደፊት ትዉልድ የማንነቱን ስረ መሰረት እንዲያዉቅ ፤እንዲያሳዉቅ እና ነፃነቱን እንዲያስጠብቅ ነዉ ፡፡

ይህም የሚሆነዉ ዕዉነተኛ እና ያን ዘመን የሚዋጂ እና የዚያን ዘመን ትዉልድ እና መገላጫዎች አሁን ላይ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡

በ18ኛዉ ክ/ዘመን የነበረዉ ተጋድሎ እና የተመዘገበዉ የኢትዮጵያ ድል የመላ ጥቁር ህዝብ ድል ብስራት አስከሆነ ይህ ትዉልድ የዚያን ዘመን ሁነት ሳይቀንስ እና ሳይልስ መዘከር አለበት ፡፡

ይሁን እና ታሪክ ሽሚያ እንጂ ታሪክ መስራት በማይችል የዘመናችን ትዉልድ ታሪክ ከማመሳቀል እና ከማቅለል ባሻገር ሌላ ማድረግ ሲቻል አይታይም፡፡

ይባስ ብለን ከሰማንያ አምስት ዓመት በፊት በሆነ የሁላችን የጋራ የነፃነት ቀንዲል በዚያ ዘመን በነበሩት በዕምየ ዐፄ ሚኒሊክ  እንዲሁም ከ ፵ ዓመት በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት አመራር እና በዘመኑ  ትዉልድ ብሄራዊ ተጋድሎ በዘመኑ የነበረዉን የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከፍ በማድረግ ነበር ፤ ነዉ ፡፡

በዝክረ አድዋ ማስታወቂያም  የኢትዮጵያ ባንዲራ ያዚያ ዘመን መሆን እንዳለበት  እና በዚያ ዘመን ከነበረዉ የኢትዮጵያ ባንዲራ ዉጭ በዚህ ዘመን መቀየር ታሪክነቱን እና ዕዉነቱን ያዛንፈዉ ካልሆነ አይለዉጠዉም፡፡

አበዉ “ማን ይናገር የነበር፤ ማን ያርዳ የቀበረ” እንዲሉ  ለዛሬ ምስክር የትናንት ታሪክ እና ዓርማ ምልክት ነዉ ፡፡ እርሱም የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ እና የዚያ ትዉልድ ዓርማ ብቻ ነዉ ፡፡ ከዚህ ዉጭ ግንጥል ጌጥ ይሆናል፡፡

 ይሁን እና ዝክረ አድዋ በሚል ማስታወቂያ ላይ የዚያን ዘመን የነፃነት እና የትግል ዓርማ የሆነዉን የኢትዮጵያ ባንዲራ /ሰንደቅ ዓላማ መጠቀም ሲገባ የኢህአዴግ ህወኃት ምልክት መጠቀም በማን እና ለምን እንደሆነ ባይታወቅም  የዚያን ዘመን ታሪክ አሻራ የዚህ ዘመን የስራ እና የትግል ዉጤት አድርጎ የፖለቲካ ድርጂት ምልክት(ባለኮከብ) መጠቀም ግን የመላዉ ኢትዮጵያ ታሪክ የሆነዉን የአንድ ዘመን የፖለቲካ ስርዓት ( ኢህአዴግ) እንዳይሆን እና ነገም ሌላ ጊዜ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ እና ታሪክን ለባለታሪክ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የ“ማዕበል ጋላቢ” መጽሐፍ ግምገማ ክፍል 1 – ገምጋሚ መንግስቱ ሞሴ (ዶ/ር)

Next Story

ከጉባኤ እስከ ጉባኤ – ፀጋ ዓራጌ ትኩየ

Go toTop