ለፖለቲካ ሴራ እንጂ ለአማራ ህዝብ ዋጋ አይሰጥም። ደመቀ መኮንን እና ቡድኑ በስልጣን ለመቆየት አማራውን የጦስ ዶሮ እያደረጉት ነው።
በኦሮሚያ ክልል በተለይ በወለጋ በሸዋ የሚገደሉ አማሮች ትኩረት እንዳያገኙ ከኦህዴድ ብልጽግና ይልቅ በደመቀ መኮንን የሚመራው የብአዴን ብልጽግና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የአማራውን ድምጽ ለማፈን ይሯሯጣል። በወለጋ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ያሉ፣ በኦነግ ሸኔ ታፍነው የተወሰዱ፣ በከበባ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ማዳን በየካምፑ ተፈናቅለው ያሉትን መርዳትና ዜጎች ለነገ ዋስትና እንዲያገኙ መስራት ሲገባ ሆን ብሎ እያስጠቃ ፣……… ሆን ተብሎ በአማራው ጭፍጨፋ ላይ የደመቀ መኮንን ቡድን በእጅ አዙር አማራን እያጠቃ ነው። በለውጡ ውስጥ ያልሰራውን ታሪክ እንደሰራ አድርጎ የሚያወራውና የሚያስወራው ደመቀ መኮንን ስሙን ለመገንባት በርካታ ገንዘብ እያፈሰሰ ነው።
ገዱ አንዳርጋቸውንና ቡድኑን ከስልጣን ለማባረር ደፋ ቀና የሚለው ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ለሚጨፈጨፉና ለሚፈናቀሉ አማሮች መብት ደፋ ቀና ቢል ኖሮ ስንት ንፁሃን ዜጎችን ባዳነ ነበር። የደመቀ መኮንን ቡድን ከሕወሓት ዘመን ጀምሮ በተላላኪነት ማገልገሉ ካለተላላኪነት መኖር እንደማይቻል አምኖ ተቀምጦ አማራን በማስጨፍጨፍ የግል ምቾቱን እየጠበቀ ነው። የሃገር ገንዘብ ዘርፎ ለመሸሽ ሲያሟሙቅ የነበረው የደመቀ መኮንን ቡድን ሕወሓት ላይ እጁን እየጠቆመ የሕወሓትን ፖሊሲ እያስፈጸመ ይገኛል። ይህ ቡድን ለአማራው ምንም የማይጠቅም የዜጎችን መብት ለማስከበርም ምንም የማይፈይድ ወራዳ ቡድን ነው። ይህ ቡድን በመላው አማራ ክልል የኦሕዴድ ብልፅግና ደህንነቶች እንዲሰማሩ በመፍቀድ እንዲሁም የመሳሪያ ማስፈታት ፕሮግራሞችን በመምራትና አርሶ አደሩን መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ነው።
አቶ ፀጋ አራጌ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሉት አቤት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ዛሬም ፍትህ እየጠየቅኩ ነው። ህግ ይከበር። ለአማራ ብልፅግና ግን ዛሬም ሌላ አንድ የህዝብ ጥያቄ አለኝ። በተለመደው ፍጥነቱ ለጥያቄዬ መልስ ይስጠኝ። የአንድ ኩንታል በወቅቱ የገበያ ዋጋ 5 ሺህ 500 ብር የሸጥከውን ——- ኩንታል ሰሊጥ ያለ ወለድ ተበደርከው? ወይንስ ለማን አከፋፈልከው? ገንዘቡ ከማንና የት እንዳለ ዛሬውኑ መልስ ለህዝቡ እንድትሠጥ እጠይቃለሁ። ከዚህ ውጭ ውርድ ከራሴ። ብለው ብአዴን የሰሊጥ ሌባ መሆኑን አጋልጠዋል።
የኦሕዴድ ብልጽግና ውሸትና የመንግስት ሚዲያዎች የሃሰት ዘገባ ተጋለጠ ! አብዛኛው የመንግስት ሚዲያዎች ዘገባዎች በውሸት የተሞሉ መሆኑ ይህ ሪፖርት አንደኛው ማሳያ ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ