ኢትዮጵያውያንን በሤራ ማንበርከክ ከቶም አይቻልም – ሲና ዘ ሙሴ

January 16, 2022

 በሀገሬ  ከሲአይኤ  ድብቅ ና ህቡ ሴራ የሚሥተካከል  ሴራ  ድንገት እየተከሰተ ለህልውናችን እጅግ አሥጊ እየሆነ መጥቷል ። የሰሞኑ ከወቅታዊው የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ የፈነገጠ ድርጊት ሁሉ ፣ ይኽንኑ ሃቅ ያደምቁልናል ።  የነጃሥ መፈታትት ፤ የፊልድ ማርሻሉ ሽልማትና የጀብዱ ሰሪዎች ሽልማት ፣ የመሥቀል አደባባይ  ሥያሜን በመነካካት ኃይማኖታዊ ጠብ ለማሥነሳት መሞከር ፤ በግባር ያለው ፋኖ ሊሸለም ሲገባው ፣ ልቡን ለማሻከር ፣ ታቅዶ ታሥቦበት የተሰነዘረ ድፍን ያለ የማፍረሥና ትጥቅ የማሥፈታት ሃሳብ ፤ ሰሞነኛ ሴራዎች እንደነበሩ ይታወቃል  ። …

ጥቂት የማይባሉ የፖለቲካ ና የኢኮኖሚ ጉዳይ ሤራዎችም ሲአዬኤ ከሚያበጃጃቸው  ከአሜሪካ ሆሊውድ ፊልሞች  የተኮረጁ ይመሥላሉ ። ” ልብ ሠቃይ ፤ (suspense )  በድርጊት የተሞላ ( Action )፤ አሥፈሪ  ወይም  ዘግናኝ  ፣ ( Horror ) በሰው የሚሰሩ  አሠቃቂ ፊልሞችን እና ብዙዎቹን የአኒሜሽን ፊልሞች ጨምሮ በተግባር በአፍሪካ ሲደገሙ ታያላችሁ ። በቤትናም ፣ በሱማሌ ፣ በግብፅ፣ በዩጋንዳ ፣ በደቡብ አፍሪካ ፤ በሊቢያ፤ በላይቤሪያ ፤ በደቡብ ሱዳን ፤ በሊባኖስ ፣ በፍሊሥጠም ፤ በኢራን ፤ በኢራቅ ፤ በአፍጋኒስታን ፤ በሶሪያ   ፤ ወዘተ የአሜሪካኑ ሲአይኤ የፈፀመውን ገድል  ና የወያኔ ዘራፊ ሠራዊት እየፈፀመ ያለውን እኩይ ድርጊት ሥታነፃፅሩ ፣ ያያችሁት የአሜሪካ አክሺን _ ሰስፔንስ ና ሆረር ፊልም ድቅን ይልባችኋል ። ( ትሪሲያ ጃንኪንሥም ቆየት ባለ ጥናታዊ ፅሑፏ ይህንኑ እውነት አረጋግጣለች ። Tricia Jenkins, The CIA in Hollywood: How the Agency Shapes Film and Television, Austin: University of Texas Press, 2012, 167 pages .)

በነገራችን ላይ ምንጫቸው ከአሜሪካ የሆነ አያሌ ዘግናኝ  ና እጅግ አውሪያዊ አጫጭር ትዕይንቶችንም በኢንተርኔት አማካኝነት ማየት ይቻላል ። ሰብዓዊነት የተላበሰ ና የሞራል ልዕልና ያለው ሰው ግን እንደዛ ያለ ሴቶችና ወንዶች የሚሰቃዩበትን ፊልም ፈፅሞ ለማየት  ህሊናው አይፈቅድለትም  ። ገና ያንን የመረጃ ጣቢያ እንደከፈተ ሊጮኽ ይችላል ። ሆኖም የሚያይ ግለሰብ እንደማይጠፋም እወቁ  ። ( ማነህ አንተ ? “ በቴንሺን ቦክሥ  “ ውሥጥ ጥግህን ይዘህ ይህንን አሥፈሪ ድርጊት በፅሞና ሥታይ የነበርከው ?  . . . )

ዛሬ የተገነዘብኩት ፣ “ እብዱ ኢሌ  “ የማሰቃያ መንገዶችን  ከዚህ ደረ ገፅ  ኮርጆ እንደሆነ ተገንዝቤለሁ ።   በሱማሊያ  እሥርቤት የማሰቃያ መንገዶቹን ( Torture way ) ከግብረ አበሮቹ ፣ ወያኔዎች ጋር የተገበረው ከዚሁ ድረ ገፅ ኮርጆ ነው ለካ !

ትላንት ና ዛሬም  ፤   በኢራቅ ፣ በሦርያ ፣ በየመን ፣ በሊቢያ ፣ በአፍጋኒሥታን ላይ   አያሌ ተመሳሳይ  ድርጊት የተፈፀመው ከሲአይኤ የማሰቃያ ዘዴ ተኮርጆ ነው ። የፀረ ቴሬሪሥት ቡድን እንቅሥቃሴን የሚተርከው ቲዌንቲ ፎር ሀወር  ፊልምም በዋናው  የሲአይ ኤ ቁንጮ   በጃክ ፖዎር አማካኝነት የታየው የማሰቃያ ዘዴ ፣ በጎንተናሞ የተተገበረ ፣ ዛሬም በሥውር በሌላው ዓለም   የሚፈፀም መሆኑንን ተረዳ ።

ወያኔም የዘርፎ በል ፣ ህሊና ቢሥ ሠራዊትን  ፣ በመንጋነት ፈጥሮ  ና ዘግናኝ የሆነ ድርጊት በመፈፀም ህዝብን የሚያሸብረው ከሆሊ ውድ ሆረር ፊልም  ዘግናኝ ማሰቃያ ድርጊትን በቀጥታ ወስዶ ነው ። በተለይም  የትግራይን ክልል ህዝብ በቁጥር ሦሥት እጥፍ የሚበልጠውን  የአማራ ክልል ህዝብን ለማሥፈራራት ፣ ጭራቅ እንጂ ፣ እንደ እሱ ሥጋ ደምና እና አጥንት ያለው ሰው እየተዋጋው እንዳልሆነ ለማሳመን  ወያኔ ፣ የሆረር ፊልምን በገሃዱ ዓለም ተግብሮታል  ። የኽ ፣ በጭካኔ የተሞላ  እጅግ የከፋ እና የከረፋ  አሥፈሪ  ድርጊቱንም ፣ ሰውን በህይወቱ እያለ  ሰውን  ቆዳውን በመግፍፍ አሳይቷል ። በመሆኑም  የወያኔ  መንጋ ሠራዊት ፣ በቃላት የማይገለፅ ፣ ህሊና ቢሥ ፣ ቦዶ ጭንቅላት ይዞ የሚጓዝ ፣ ከእንሥሣት በታች የሆነ   ፣ ለሆድ ብቻ  አሳቢ ሆኗል ። የሚመራው አካልም ነጭ ጅብ ሆኖበታል ።   ለሠላም ፣ ለፍቅር ፣ ሰው ባለው አጭር ዕድሜ በሥቃይ እንዲኖር የሚፈልግ ከመሆኑም በላይ የትግራይ ጭቁን ህዝብን በሆዱ የሚገዛ አረመኔ ነው ። ዘላዓለም ዓለሙን ከችጋር ና ከችግር እንዳይወጣ በፈረንጅ ሥንዴ እየገዛው የዋህ ና ያልተማረውን ሥለ አለም ፖለቲካ ምንም እውቀት የሌለውን ፣ ህዝብ ከወንድም ና እህቱ ጋር ደም አቃብቶታል  ።

በነገራችን ላይ ፣  በዚህ መራራ ና በግፍ የተሞላ ጦርነት የአማራ ና የአፋር ክልል ዜጎች ክፉኛ ተጎድተዋል ።  ደግምም በዚህ ህሊና ቢሥ ነፍሰ ገዳይ የትግራይ ወራሪ ቡድን ጥቃት ና ውድመት እንዳይደርስበት በክልል መንግሥት ደረጃ ፣ በልዩ ኃይል ታቅፎ  በሚገባ ሠልጥኖ ፣ የአማራ ፋኖ እና የአፋር ወጣት ራሱን ለመከላከል 24 ሰዓት ዝግጁ መሆነ አለበት ።” የመሐል አገር ሰው በሴትና በሥጋ ይታለላ ። ያለው ማነው ? “ ኦሮማይ !

የትግራይ ጭቁን ህዝብ በጨካኙ ነጭ ጅብ ( በደብረፅዮን እና ሰው አራጅ ጓዶቹ ) ታግቶ ፣ የጥይት ራት እየሆነ ነው ። ቀን በማይሰጠው ሆዱ መገዛት ፣ ወይም በርሃብ መሞት ምርጫው ሆኗል ። ሰብዓዊ ክብሩ ፣ ቢላ ይዞ በሚያሥፈራራው  በጨካኙ  የደብረ ፅዮን ገዳይ ቡድን ተገፏል ።  ሳይወድ በግዱ  ፣ ከአገራባች ወንድምና እህቱ ጋር ደም አቃብቶታል ። በርሃቡ ሰበብ ፣ ሆዱን እያየ  ወደገደል እንዲጓዝ በሐሰተኛ ትርክት  እየተደረገ ነው ።  ወያኔ  / ትህነግ  የሆሊ ውድን  ዘግናኝ የሆረር ፊልም  ድርጊት በወጉ በመኮረጅ ፣ ይኽንን ቅን ህዝብ በሆዱ ገዝቶ ፣ ሳይወድ  ሰውነቱን አሥረሥቶ ለሆዱ ና ለሆዱ ብቻ እንዲያሥብ በማደረግ በያዘው ቢላዋ እያሥፈራራ ባርያው አድርጎታል  ።

የቢላውን ሥለት እያየ ፣ አንገቱ ላይ እንዳያርፍ እየፈራ ፣ ህዝብ ፀጥ ለጥ ብሎ የሤጣን ድርጊቱን የሚፈፅመው  ፤ ደብረፅዮን ፣ በጭካኔው ከታወቀው ከአዶልፍ ሂትለር ፣   መቶ እጅ የከፋ መሆኑንን በመገንዘቡ ነው ። የተጨቆነው ፤ በአፈሙዝ ሥር ያለው ፤ የትግራይ ህዝብ ፤ ነፃ የሚያወጣው ጀግና ኢትዮጵያዊ ይፈልጋል ። እናም እንዲህ ይላል …

” እነ ‘ ጃሥን ‘ የሚፈታ ኢትዮጵያዊ መንግሥትን አናወድሥም ።   ራሳችሁ ፣ በፍርሃት ቆፈን ተይዛችውና ለእናት አገራችሁ ፣ በጀግንነት ለመሞት ባለመፈለጋችሁ ፣ ለዚህ ድብቅ ፍርሃታችሁ ፣ የካድሬ ትንተና በመሥጠት ፣ባላለቀ ጦርነት በድል አድራጊነት በመሥከር  ያለ ወቅቱ  ከምትገባበዙ ና ጀግናውን የኢትዮጵያ ህዝብ  የጋለ ወኔውን ከምታቀዘቅዙት  ፣ በታላቅ ሴራ እጃችን አልታሰረም ካላችሁ ፣ ወኔው ፈፅሞ ከመብረዱ ና እናንተም ውድቀታቸው ከመቃረቡ በፊት ፣  እሥቲ ወደ ትግራይ ግቡና እያንዳንዱ የደብረፅዮንን ልዩ አራጅ  ሽፍታ ፣ ለቃቅማችሁ  ተገቢውን ቅጣት ሥጡት !!!  ያን ጊዜ  እኛም ፣ በየቤቱ የተወሸቀውን የልጆቻችንን  ለከንቱ ዓላማ  አሥጨረሻ  አጋልጠን እንሰጣችኋለን  ።

አይ አንዋጋም ።በውሥጣችን የመሸጉትንም ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ አናቀርብም  ብላችሁ ፣ ከደብረፅዮን ቡድን ጋር  ውሥጥ ፣ለውሥጥ  የምታደርጉት  እርቅ ከቀጠላችሁ  የእኛም ጠላቶች መሆናችሁን እወቁት  ። እኛ የምንፈልገው ከጠመንጃ አፈሙዝ ነፃ መውጣት ነው ። እኛ ከጠመንጃ አፈሙዝ ነፃ ካልወጣን በሥተቀር በመላው ኢትዮጵያ የጠመንጃ አፈሙዝ አገዛዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለን እናምናለን  ።እኛ የምንፈልገው ፍትህ እና እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ነው ። አማራ ወይም ኦሮሞ አልያም ትግሬ ትልቅ ሆኖ ሌላው ዜጋ ትንሽ የሚሆንባትን አልያም በአገሩ እንደ ሁለተኛ ና ሦሥተኛ ዜጋ የሚቆጠርባትን የዘውግ ሥርዓት የነገሰባት ኢትዮጵያን ዳግም በኦሮሙማ አማካኝነት ሲደገም ማየት አንፈልግም ።  እኛ የምንፈልገው እንደ አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ሩሲያ ፣ አሜሪካ፣ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ኪኒያ ፣ ጋና ፣ ደቡብብ አፍሪካ ፣ እሥራኤል ፣ ስፔን ፣ ቱርክ ወዘተ ። የሠለጠነ የዜግነት ክብር ያለበት መንግሥት ነው ። ለሥጋ ምቾቱ ፤ ለሁሌም ብፊ ምግቡ ፤  ለቮድካ ና ለውሥኪው ፤ ወዘተ ። ሲል የነገድ ፣የዘውግ ና የወንዝ ፖለቲካን እንደዘመናዊነት ሊሰብከን የሚፈለግ ድንዙዝ ካድሬ  በነጋ በጠባ ቁጥር በለከት አልባነት በምላሱ ሆዳችንን እየነፋ ፣ ኢትዮጵያን …  እንዲያሥተዳደር አንሻም ። … የነደብረፅዮን ቡቹሎች በየሣተላይቱ  በውሸታቸው የሚያደነቁሩን ይበቃናል ። “

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እንደ ኢትዮጵያዊ ካለፈው ምን ተማርን? ለመጭው ትግልስ የምን ያህል  እየተዘጋጀን ነው? —ፊልጶስ

Next Story

መከላከያው ተቋማዊ ወይስ ኔትዎርክ – ከፍትህ መጽሔት የተወሰደ – በተመስገን ደሳለኝ

Go toTop