ጀግኖች እነ ማን እንደሆኑ፣ ማን ምን እንዳደረገ ሕዝብ ያውቃል። ለጀግና ዕውቅናም ሆነ ሽልማቱ የሕዝብ ክብር ነው!! ብ/ጀኔራል ሻምበል በየነ – ባለከዘራው የነ ዶር አብይ ሽልማት አያስፈልገው። ሕዝብ ያከበረው በልቡ የሸለመው የመከላከያ መኮንን አባል ነው።
“ጀግና ሞትን የማይፈራ ነው”
ደራሲ ብርሃኑ ዘሪሁን
የሆነው ሆኖ ባንዳ ሲያፍር ይኖራል፤ ጀግና በተጋድሎው የዛሬንና የመጭውን ትውልድ አንገት ቀና ያደርጋል።
የሕዝብ ሥነ-ልቦናዊ ከፍታ ምንጩ ሞትን የናቁ ጀግኖች ናቸው!! እንደሆነብን ሁሉ ዛሬ እግራቸው ስር በወደቅን ነበር ምናልባት ሸብረክ ማለታችን የመስፈንጠሪያው አስገዳጅ ሁነት ስለሆነ ነው።
ከሕይወት በላይ ‘ክብር’ ዓላማ መሆኑን በተግባር መግለጥ በፎቶ ሲነበብ ሰውየውን ይመስላል!!
የታሪክ ሽሚያ ውስጥ የገቡ ‘የትንሽነት ኃይሎች’ ሐሰን ታንታዊ’ያቸውን ፈጥረዋል። እኛ ግን በተግባር ተፈትነው የማይሞት ታሪክ የሰሩ የሕዝብ ልጆችን የትውልዱ መማሪያ እናደርጋለን። እነርሱም ሆነ ጠላት ሰውየውን ያውቁታል። ገጽታው በራሱ ችግሮች ሁሉ ከሞት በታች ናቸው የሚል ሞትን የናቀ ወንድነቱን ይመሰክራል!! ሰውዬው ለጀግንነቱ ዕውቅናም ሆነ ሽልማቱ የሕዝብ ክብር ነው!!
ሕዝብ በፖለቲካ ሳይሆን በተግባር ያነግሣል! ታሪክ ይዘክራል! ፖለቲካ የሰቀለውን ጊዜ ይጥለዋል፤ ሕዝብ ያነገሠውን ግን ታሪክ አይጥለውም!
ወደር የሌለው የሕዝብ ልጅ
ብ/ጀኔራል ሻምበል በየነ – ባለከዘራው
©ሙሉአለም ገ.መድህን