በቻልነው አቅም ሁሉ ከህዝባችን ጎን ነን – ወርቁ አይተነው

December 13, 2021

አሁን ያለንብት ስአት የመተሳሰብ የመረዳዳትና ለተቸገረው ወገናችን የመድረስ ግዴታችን እምናሳይበት ወቅት መሆኑን በመረዳት ላለፋት 3 ቀናቶች ወደ ቤንሻንጉል ክልል አምርቻለሁ።

ለመጭው 3 ወር እንዲደርስ እና ለምወደው ለማከብረው በጦርነቱ ለተፈናቀለው ብሎም በጦርነቱ ምክንያት ህውኃት ሀብት ንብረታቸውን ዘርፋ ባዶ ቤት ላረገችው ማህበረሰብ የቻልኩትን ያክል ለማገዝ እንዲሁም መልሶ መቋቋሙ በተቻለው መጠንም እንዲፈጥን ለማረግ እራሴ በአካል በመገኘት እንደ ቆላ ስንዴ እና ሌሎች ተዛማች የሆኑ የእህል አቅርቦት ለወገኔ በፍጥነት ለማድረስ በሞቀታማው በርሀ እርሻ ቦታ ተገኝቸ ሁኔታወችን እያስተባበርኩ እገኛለሁ ።

እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ባህላችንን ከቅድመ አያቶቻችን እንደወረስነው ሁሉ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ 1 ለራሴ 3 ለተጎዳው ወገኔ የሚለውን እሳቤ በህሊናችን ውስጥ በማስገባት ይህን መጥፎ ግዜ በመተባበርና በመረዳዳት ከወገናችን ጎን እንሁን እላለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ወርቁ አይተነው

ይህ ከ 177 ,000 በላይ ተከታይ ያለው ፔጅ ትክክለኛው ፔጃችን ነውና ተመሳስለው በተከፈቱ ፔጆች እንዳትሸወዱ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በልጠን ካልተገኘን….!!! – ቹቹ አለባቸው

Next Story

የብርሃን አካል በሆኑ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት የአንድነት፣ ነጻነትና ፍቅር ፍሬዎች ይጎመራሉ – ሚኪያስ ግዛው

Go toTop