የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

December 10, 2021
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

-አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

ታህሳስ 01 ቀን 2014 (ኢዜአ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዝግጅት! ለማን? – ቴዎድሮስ ጌታቸው

Next Story

የስድስት ወር ነፍስጡር እናትና ልጇን አላስደፍርም ያለ አባት – የቀን 7 ሰዓት አማርኛ ዜና … ታህሳስ 1/2014ዓ.ም

Go toTop