የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ የውብዳር መሀመድ የሽብር ቡድኑ ከተላላኪው ሸኔ ጋር በመተባበር ከተማዋን አውድሟታል ይላሉ።
“ሐብትና ንብረት ይተካል” የሚሉት ወይዘሮዋ ወራሪው ንጹሃንን በአደባባይ በመረሸን የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ወራሪዎች መነኩሴ ሳይቀር በመድፈር ነውረኝነታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት።
“የትግራይ ወራሪዎች አንዲትን ሴት ስምንት ሆነው በመድፈር ለሰው ልጅ አዕምሮ የሚከብድ ኢ-ሠብዓዊ ድርጊት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።