ጠመኔ ጥለው ክላሽ የነሱት መምህራን!

November 4, 2021
ማተቤ አያሌው እና ማሩ አንተነህ ር/መምህራን ናቸው። የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል። እንዳሻው አቤ ደግሞ መምህር ነው። ሁሉም ቀጣዩን ትውልድ በመቅረፅ ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል።
አሁን ግን ትምህርትን የሚያስተው ሌላ ጉዳይ መጥቷል። እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማትን የሚዘርፍ፣ ተማሪዎችን የሚጨፈጭፍና የሚጎዳ ጠላት መጥቷል። ስለሆነም ጠመኔያቸውን ጥለው ክላሽ ይዘዋል። የመምህራን መለዮ ልብስን ትተው የታጣቂ መለዮ ለብሰዋል።
መምህራኑ የምዕራብ ጎጃም ዘማቾች አባል ሆነው አጥፊውን የትግሬ ወራሪ ኃይል ለመፋለም ግንባር ተገኝተዋል።
መምህራኑ ማስተማርን የሚወዱት ስራ ይሆናል። ይሁንና አሁን ጠመኔያቸውን ጥለው ክላሽ እንዲይዙ የሚያስገድድ ጠላት መጣ። ለሰራዊቱ ብቻ ተትቶ ዝም የማይባል ጨፍጫፊ፣ አውዳሚ፣ ዘራፊ የሕዝባችን የዘላለም ጠላትን ስራን ትቶ መፋለም እንደሚያዋጣ ተረድተው ዘመቱ።
የትግሬ ወራሪ ኃይልን መፋለም የመጨረሻው ሰብአዊ ተግባር ሆኗል ብለዋል። ትውልድን የምንቀርፀው በሕይወት፣ በሕልውና ሲኖር ብቻ ነው ብለው አምነዋል።
አደባባይ ሜድያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መዋቅር እና አደረጃጀት መመሪያ

Next Story

በክልሉ ከአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Go toTop