በአዲስ አበባ ከተማ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ20ሺ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡
የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባሎችም ድርሻ የጎላ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በማሰራጨት ለሽብር አላማ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ የጦር መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ያሉት ሃላፊው ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ነው ማለታቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃያሳያል።
የሽብርተኛ ቡድኖችን ተልዕኮ ለመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህዝቡ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመላክቷል፡፡
(ኢ ፕ ድ)