![tplf](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2021/08/TPLF-1-720x540.jpg)
1. ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመክፈት በመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ እና ኢትዮጵያ አሉኝ በምትላቸው ረዥም ርቀት ተወንጫፊና ወሳኝ ከባድ መሳሪያዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። የሰራዊቱ አባላትን በብሔር ለይቶ ረሽኗል። የአማራና ኦሮሞ ተወላጆችን በቀዳሚነት ለይቶ በማንነታቸው ገድሏል፡፡ በሰሜን ዕዝ ላይ እጅግ አስከፊ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅሟል፡፡
2. ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ ከ1 ሺህ 600 በላይ የአማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል።
3. ህዳር 3/2013 ዓ.ም ወደ አማራ ክልል ባሕር ዳር እና ጎንደር በተመሳሳይ ህዳር 4/2013 ዓ.ም ወደ ኤርትራ፣ ሮኬቶችን ተኩሷል፡፡ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል፡፡ ሕዝብንም አሸብሯል። ኢትዮጵያን እንደሀገር ክዷል፤ ጎረቤት ኤርትራን ሉዓላዊነት ተዳፍሯል፡፡
4. ግምቱ በውል ባልታወቀ የኢትዮ ቴሌኮም የንብረት ዝርፊያ፣ የገቢ ኪሳራ እና በስራ ላይ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኛ ግድያ እና አፈና ተፈፅሟል፡፡
5. ህዳር 14/2013 ዓ.ም የአክሱም ኤርፖርትን ሙሉ ለሙሉ አውድሟል፡፡ በዚህም በመቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀገራዊ ኪሳራ አድርሷ፡፡
6. ህዳር 08/2013 ዓ.ም በሁመራ ከተማ የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጅ ባለሀብቶችን በማንነታቸው ብቻ ከሁመራ ከተማ አፍኖ በመውሰድ ‹እድሪስ› በተባለ አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ጫካ ላይ ጥሏቸዋል።
7. ሰኔ 17/2013 ዓ.ም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኀላፊ እምብዛ ታደሰ ከመቀሌ ከተማ አፍኖ በመውሰድ ‹አይደር› በሚባል አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው አካሉን ቆራርጠው ጥለውታል። በዚህ መሰሉ የጭካኔ ግድያ ከአርባ በላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩን አመራሮች ገድሏል፡፡
8. ህዳር 7/2013 ዓ.ም አራት በትግራይ ክልል ዋና ዋና ድልድዮችን አፍርሷል።
9. ሰኔ 1/2013 ዓ.ም በጸጥታ ካምኘ የሚገኙ 300 የኤርትራ ተወላጅ ስደተኞች በመጠለያ ካምፓቸው በመግባት ረሽኗል።
10. የዓለም አቀፉ ቀውስ ኮሚቴ IRC ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም እንደገለፀው አንድ የቡድኑ አባል መገደሉን፣ የስደተኞች ምክር ቤት (DRC) ደግሞ ታህሳስ 3/2013 ሁለት አባላቱ መገደላቸውን፤ ሰኔ 17 እና 18 አካባቢ ሦስት የድንበር ተሻጋሪ ሐኪሞች (MSF) አባላት መገደላቸውን ገልፆል። የእርዳታ ሠራተኞቹ የተገደሉት በአሸባሪው ትህነግ ነው።
11. የካቲት 10/2013 ዓ.ም የታጠቁ የትህነግ አባላት በፈፀሙት ጥቃት አዲ መሲኖ በተባለ አካባቢ በአውቶቡስ የተሳፈሩ መንገደኞች ላይ በተከፈተ ተኩስ በርካቶች ተገድለዋል፡፡
12. መሰረታዊ የአገልግሎት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ዝርፊያ ተካሂዷል። የመብራት አገልግሎት ማቋረጥ፣ የባንክ ዘረፋ ማካሄድ፤ ለተረጅዎች የሚላኩ የሰብዓዊ እርዳታን ዘርፏል።
13. የካቲት 12/2013 ዓ.ም የትግራይ እንደርታ ተወላጅና የፈንቅል ንቅናቄ መሪ የነበረውን የማነ ንጉሴን ‹በሔዋነ› አካባቢ ተገድሏል፡፡
14. ትህነግ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈፀመ ቀን ጀመሮ ትህነግ በጀመረው ጦርነት ምክንያት በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመውና የሚደርሰው ወሲባዊ ጥቃትና የአስገድዶ መድፈር ተፈፅሟል። በርካታ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
15. ትህነግ ሚያዚያ 05/2013 ዓ.ም ትግራይ ላይ ጥቅምት 24 ላይ የፈፀመውን አይነት ጥቃት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ እንዲፈፅም አድርጓል። ይህን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈጸመው ከቅማንት ኮሚቴ የሽብር ቡድን ጋር በመሆን ሲሆን፤ ጥቃቱ ጭልጋ ከተማ ላይ በሰፈረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና በአማራ ልዩ ኀይል ላይ ነበር የተፈጸመው፡፡ በተጨማሪም በግዳጅ ወገንህን ካላጠቃህ እያለ ሰላማዊውን የቅማንት ገበሬ በመከላከያና በአማራ ልዩ ሃይል ላይ ጦርነት ክፈቱ እያለ ሲያሰቃይ ከርሟል።
16. አፋር ክልል ጋሊኮማ ተፈናቃዮች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የነበሩ ንጹሐን ላይ በፈፀመው ጥቃት 107 ሕጻናትን ጨምሮ ከ240 በላይ ንጹሐንን ጨፍጭፏል።
17. በራያ መሆኒ ከተማና አካባቢው ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ንጹሐንን ገድሏል። ሙስሊሞችን ብቻ ለይቶ የጨፈጨፈው በሀገሪቱ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዲነሳ በመፈለጉ ነበር፡፡
18. በነሐሴ/2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን አጋምሳ በተባለ ቦታ በከባድ መሣሪያ በመደብደብ የአንድ መንደር ንጹሐንን ገድሏል። የአጋምሳው ጭፍጨፋ ትህነግን በጦር ወንጀለኝነት እንደሚያስጠይቀው The Telegraph ከሰሞኑ በሠራው ዘገባ አስነብቧል፡፡
19. በወረራቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ቤት ለቤት በመዞር ባለሀብቶችን፣ ወጣቶችን ፣ አመራሮችን፣… ወዘተ ገድሏል። የአዕምሮ ህሙማንን “ሰላዮች ናቸው” በማለት በአደባባይ ረሽኗል።
20. በወልዲያ ሆስፒታሉን፣ ስታዲየሙን፣ ዩኒቨርስቲውን፣ በመርሳ ከተማ የሚገኘውን ቅርንጫፍ ካምፖሱን ጨምሮ ከሹካና ማንኪያ እስከ መኪናና ኮምፒውተር ድረስ ዘረፋ ፈጽሟል፡፡ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን ጨምሮ ቁልፍ የማህበራዊ ልማት ተቋማት ንብረታቸው ተዘርፎ ባዶ ሕንጻቸው ቀርቷል። በተመሳሳይ በወልዲያ መምህራን ኮሌጅ፣ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ሙሉ በሙሉ ንብረቶች ተጭነው ተወስደዋል።
21. በሰቆጣ ከተማ ከፍተኛ ዝርፊያ ፈጽሟል፡፡ በዘረፋው በሌሎች ከተሞች ላይ እንዳደረገው ቁልፍ በሆኑ ማኅበራዊ ልማቶች ላይ አተኩሯል፡፡ በዚህም ተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታል፣ ሰቆጣ መምህራን ኮሌጅ፣ አመልድ፣ እርሻ ምርምር፣ ቴሌ-ኮምዩኒኬሽንና የግሉ ዘርፍ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ውድመትና ዘረፋ ፈጽሟል፡፡
22. ወልድያ ከተማ ከዝርፊያ በተጨማሪ በከባድ መሳሪያ ድብደባ ንጹሐንን ገድሏል፡፡
23. በሰሜን ወሎ እና አፋር 700 ሽህ የሚጠጋ ሕዝብ አፈናቅሏል፡፡
24. ነሐሴ 13/2013 በደብረታቦር ከተማ ላይ አምስት መድፍ በመተኮስ የሲቪሊያን መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት አድርሷል፡፡ በዚህም ሙሉ ቤተሰብ ገድሏል፡፡
25. በላሊበላ፣ ቆሞ፣ ጨጨሆ፣ መርሳ፣ ማይጠብሪና ሌሎች አካባቢዎች የመንግሥት ተቋማት፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ የግለሰብ ንግድ ቤቶችና የግለሰብ ቤቶች ተዘርፈው ንብረታቸው ወደ ትግራይ ተጭኗል።
ለኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች መብት ታግያለሁ በሚል አፋዊ ድስኩር ይታወቅ የነበረው አሸባሪው ትህነግ በተጨባጭ የብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ስለመሆኑ በግብሩ አሳይቷል፡፡ የመላ ኢትዮጵያውያን ውህድ ማንነት የሆነውን መከላከያ ሠራዊታችንን በመውጋት ጫፍ የወጣ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጥላቻ እንዳለው ያረጋገጠው አሸባሪው ትህነግ፣ አሁን ደግሞ በአማራና በአፋር አዋሳኝ አካባቢዎች እየፈጸመ ያለው አውዳሚ ተግባራቱ ማንነቱን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህ ሰይጣናዊ ግብሩ ማርከሻ የሆኑት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ ክንዳቸው ዘምተውበታል፡፡