ዛሬ በዚህ መድረክ ለመገናኘታችን መነሻ ምክንያት የሆነው የሰማዕት ወንድሞቻችን የትግል ዓላማ ውርስ ጉዳይ ነው፡፡ የትግላችን መነሻ ቀዳሚ ሥረ-ምክንያት ደግሞ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) ብሎ የሚጠራው ቡድን እና አስተሳሰቡ ነው፡፡
ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተነሳው ይህ ድርጅት፣ በተለይም የአማራን ህዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ የተነሳ በመሆኑ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የአማራ ሕዝብ የመከራ ምንጭ ሁኖ ቆይቷል፡፡ ትህነግ በአማራ ቁልቅለት የምትጸና ታላቋን ትግራይ ለመፍጠር ሲል አማራን በጅምላ ገድሏል፤ አሰድዷል፤ ወደእስራትም አግዟል፤ ግዛቱን በመውረር ለሦስት አስርት ዓመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል፡፡ ለዚህ ማሳያው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ላይ የፈጸማቸው የሠላሳ ዓመታት ተጨባጭ ወንጀሎቹ ህያው ምሳሌ ናቸው፡፡ ዛሬም ከዚሁ ደመኛ ታሪካዊ ጠላትነቱ አልታቀበም፡፡ እንዴውም የአማራ ግዛቶችን በዳግም ወረራ ለመቆጣጠር በከፈተው ጥቃት በህዝባችን ላይ የህልውና አደጋ ደቅኗል፡፡
በግልጽ እንደሚታየው በምስራቅ አማራ ማለትም ወሎ እንዲሁም በምዕራብ አማራ በጠለምት ግንባር አልፎም በአፋር ግንባሮች ህፃናትንና አዛውንቶችን ከፊት የጥይት ማብረጃ በማድረግ ከኋላ በታጠቀ ኃይሉ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል። ዕድል ካገኘ የራሱን ሀገር ከመመስረቱ በፊት ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዋነኛ ግቡ ነው፡፡ መቼም ቢሆን መዘንጋት የሌለበት ቁምነገር ትህነግ በአማራ መቃብር የምትጸና ታላቋ ትግራይን መመስረት የምንግዜም ግቡ ስለመሆኑ ነው፡፡
ለዚህ ግብ ስኬት ደግሞ ከዲያስፖራ እስከ ሀገር ቤት፤ ከእረኛ እስከ ምሁር፤ ከቄስ እስከ ሼኽ ድረስ የትግራይን ሕዝብ አሰልፈዋል፡፡ እነሱ እንደሕዝብ ነው እየወጉን ያሉት፡፡ በድርጅት እና በሕዝብ መካከል አንድም ልዩነት የለባቸውም፡፡ አማራን እንደሕዝብ ኢትዮጵያን እንደሀገር በጠላትነት ፈርጅው ሊያጠፉን ተሰልፈዋል፡፡ ታዲያ እነሱ በዚህን ያህል መጠን ለጥፋት ሲዘጋጁ እኛ ራሳችን፣ ሕዝባችንና ሀገራችንን ለማዳን ምን ማድረግ አለብን?
በእኛ እምነት ከተጋረጠብን የህልውና አደጋ በድል ለመሻገር የሚከተሉትን አምስት ነጥቦች የጋራ አቋም ወስደን መተግበር ይኖርብናል!
1ኛ) አንድነት ወሳኝ ጉዳይ ነው። የአማራ ሕዝብ ጥንተ-ጠላት የሆነው ትህነግ ከፋፋይ አጀንዳዎችን እየሰጠ ሊያጠቃን ይፈልጋል። እና ግን አንድነት ኃይላችን ስለመሆኑ ከአባቶቻችን ትምህርት ወስደናል። የትኛውንም የፖለቲካም ሆነ ሌላ ልዩነት ወደጎን በመተው እንደሕዝብ ሊጨፈጭፈን አቅዶ የመጣውን አሸባሪ ኃይል መታገል አለብን። የተኳረፈ ኃይልን በማስታረቅ፣ በአሉባልታና መሰል ነገሮች የሚሰሙ ልዩነቶችን በመፍታት ሙሉ ትኩረታችን፤ ሙሉ አቅማችንን እንደሕዝብ ሊያጠፋን እየመጣ ባለው ትህነግ ወያኔ ላይ ማድረግ አለብን። ገዥ ፓርቲ፣ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳንል፣ የኃይማኖትና መሰል ልዩነቶች ሳይበግሩ በጋራ መቆም አለብን። የአማራ አንገቱ አንድ ነው! ይህንንም በተግባር እናስመሰክራለን!!
2ኛ) ትህነግ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግሬ ወጣቶችን በማሰለፍ በአስከሬን ተረማምዶ አማራን እንደሕዝብ መፍጀት ይፈልጋል። እስካሁን ከቋጠረው ጥላቻ በተጨማሪ ተረማምዶት ለሚመጣው የትግሬ ወጣት ባለ ዕዳ የሚያደርገን እኛን አማራዎችን ነው። አሸባሪው ትህነግ ‹‹ሒሳብ ማወራረድ›› የሚለው የሽብር ፕሮፖጋንዳው ሲተረጎም እንደአማራ ሕልውናችን ማጣት፣ እንደሕዝብ መጥፋት ማለት ነው። ነገ ቢያሸንፍ ሴቶቻችን ደፍሮ፣ ወንዶቻችን ገድሎ፣ ትውልዱን ከማንነቱ ውጭ አድርጎ ከማጥፋት አይመለስም፡፡ ይህን የከፋ ደመኛ ጠላት ባለበት ለመቅበር የትውልድ ግዴታ አለብን፡፡ እህቶቻችን እንዳይደፈሩ፣ እናቶቻችን እንዳያለቅሱ፣ ወንዶቻችን እንዳይኮላሹ፣ ቀጣዩ ትውልድ ማንነትና ሀገር ተነጥቆ እንዳይኖር ዛሬ የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ በቁርጠኝነት መነሳት አለብን፡፡ ስለሆነም የአማራ ልዩ ኃይልን፣ ሚሊሻውን፣ ፋኖን (በጥቅል ስያሜቸው የአማራ ሕዝባዊ ኃይልን) እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል መታገል ብቸኛው አማራጫችን ነው። ዛሬ ቆመን እያየን የሚመጣ ኀይል ነገ እኛን ወደመቃብር ከማውረድ አይተወንም። በታሪክ ተጠያቂ፣ ተዋራጅ እንዳንሆን ከአሁኑ ትውልዳዊ ግዴታችን መወጣት ይኖርብናል። ትህነግ ከልጅ እስከ አዋቂ አዝምቶ ሀገርና ሕዝብ ለማጥፋት ሲሰራ እኛ ሀገርና ሕዝብ ለማዳን መዝመት ግዴታችን ነው። ልጆቻችን እንዳይወቅሱን ከአሁኑ ግዴታችን እንወጣለን!
\
3ኛ) አሸባሪው ትህነግ ጥቃት የሚጀምረው ከአካባቢያችን ነው። አካባቢያችን ከጥቃት፣ ከሰርጎ ገብ እንዲሁም ከውስጥ ባንዳ አካባቢያችን መጠበቅና ማጽዳት አለብን፡፡ ከመንግስት ፀጥታ ኃይልና ከሕዝባችን ጋር ሆነን በንቃት እንጠብቃለን። በዚህ ሂደት ለሀሰት መረጃ አንሸበር። ትህነግ መቀሌን ለቅቆ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ እንደገና ተመልሶ አይተናል። ትህነግ ሕዝቡን እያስራበ፣ በብዙ እጦት ውስጥ ሆኖ እኛን ለማጥፋት አቅዶ አሸባሪና ወራሪ ኃይል እያሰማራብን ይገኛል። ድሮ ብሔር ብሔረሰቦችን እርስ በእርስ እያጋጨ የነበረው ኃይል፤ አሁን ብሔር ብሔረሰቦች እውነታው ሲገባቸው በአንድ ላይ ልዩ ኃይላቸውን አዝምተውበታል። እንደ አንድ ኢትዮጵያ ሕልውናችን ለማስቀጠል የጋራ ትግል እናደርጋለን፡፡ እንደአማራ ከድሮው የተሻለ አደረጃጀት አለን፡፡ በብዙ መልኩ የተሻልን ነን። ይህን አጋጣሚ ካልተጠቀምን ግን አለን የምንለውን ታሪክ፣ እሴት፣ ሀብት፣ ጸጋ፣… ሁሉ ያጠፋል። ትግሉ ለመጥፋት መፍቀድና አለመፍቀድ ነው። ከማሸነፍ ውጭ አማራጭ የለንም። ለማሸነፍ ደግሞ ያለንን ማወቅ ያስፈልጋል። ንቁ መሆን፣ በፕሮፖጋንዳ አለመሸበርና እንደአባቶቻችን በዓላማ መጽናት መታገል ይኖርብናል!!
4ኛ) ትህነግን ለመፋለም ቤተሰቦቻቸውን ወደ ግንባር የላኩ ወገኖቻችንን ማገዝ፣ ማበረታታት አለብን። ቤተሰቦቻቸው መስዋዕትነት ለመክፈል ቀድመው የተገኙት የእኛን ሕልውና ለማስጠበቅ በመሆኑ የዘማች ቤተሰቦች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ቅድሚያ እንዲያገኙ ልዩ ማበረታቻ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
5) የፀጥታ ኃይላችን በሞራል፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ መደገፋችንን እንቀጥላለን። ዋጋ እየከፈለ ያለው ለእኛ ሕልውና ነውና የትኛውንም የጸጥታ ኃይል መደገፍ ሕልውናችንን የማስቀጠል አንዱ የድጋፍ ስልት ነው፡፡ የገንዘብ ድጋፉ የአማራ ክልል መንግሥት የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ባዘጋጃቸው ሕጋዊ የባንክ የሒሳብ ቁጥሮች ብቻ ገቢ የሚሆን ሲሆን፤ በአይነት የሚደረገው ድጋፍ በተለይም ከምግብ አቅርቦት ጋር የተያያዘው ድጋፍ የሁሉንም ቤት የሚያንኳኳ ነው፡፡ ሁሉም እንደየ አቅሙ ደረቅ ሬሽን ጨምሮ በግ፣ ፍየል፣ በሬ ወደ ግንባር በመላክ ለሕዝባዊ ኃይላችን ያለንን ወገናዊ ፍቅር ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡
6ኛ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ የአማራነት አጀንዳ ፋይሉ የተዘጋ ነው፡፡ የአማራ ድንበሩ ተከዜ እና አሸንጌ ሀይቅ ድረስ ነው፡፡ ወትሮም ቢሆን ትግሬ እንጅ ትግራይ ተከዜን ተሻግራ አታውቅም፡፡ ዛሬም ይህንኑ ታሪክ በሕዝባዊ ትግላችን እናጸናዋለን፡፡ ለዚህም በሰማዕታቱ ስም ቃል እንገባለን፡፡
በመጨረሻም የአማራ ሕዝብ ብቸኛው አማራጫ ማሸነፍ ብቻ ነው። ተሸንፈን በሕልውና እንደማንኖር እያወቅን ሽንፈትን ልናስብ ፈጽሞ አይገባም። አሸባሪው ትህነግን ጫካ ሆኖ ብቻ ሳይሆን ቤተ-መንግስት ሆኖም ነሐሴ 01/2008 በመሰሉ የተጋድሎ ቀናት በመስዋዕትነታችን ቅስሙን የሰበርን ጀግና ሕዝብ ነን! ዛሬም ታሪክ ከመስራት የሚያግደን አንዳች ኃይል የለም፡፡
አማራ በመራር ተጋድሎው በጥንተ-ጠላቱ ትህነግ መቃብር ላይ የመጨረሻውን ሳቅ ይስቃል!!
“ክተት መክት ፤ ለፍትህ ለነጻነት”
“አሸባሪነት ይቀበራል፤ ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል”
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለአማራ ሕዝባዊ ኃይል እና
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰማዕታት!!
ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም.
ወልቃይት-ሁመራ
አማራ-ኢትዮጵያ