ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተወዳደሩ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ መቀመጫ ያገኘ ፓርቲ መንግስት መመስረት እንደሚችል ይታወቃል።
የምርጫውን የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የሲቪክ ማህበራት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ውጤት ይፋ አድርገዋል።
ዛሬ ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት መሰረት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመቀመጫ ብዛት 484 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 410 መቀመጫ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል።
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብን 5፣ ኢዜማ 4፣ የግል ተወዳዳሪዎች 4 እንዲሁም የጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 ወንበር ማግኘታቸው ይፋ ሆናል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 547 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት አብላጫ መቀመጫ ያገኘ ፓርቲ መንግስት ይመሰርታል።
የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ
ሐምሌ 03 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ዛሬ ሃምሌ 3 ቀን 2013 ዓ.ም የስድስተኛው አገራዊ የምርጫ ውጤት በአዲስ አባባ ይፋ አድርጓል።
በመድረኩም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የሲቪክ ማህበራት ታድመዋል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ፣ የክልል ምክር ቤቶችን የምርጫ ወጤት ይፋ አድርጓል።
አዲስ አበባ
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 138
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 10
ብልጽግና ፓርቲ ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 138
ድጋሚ ምርጫና ቆጠራ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልል የለም።
አማራ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ – 294
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 125
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 128
አብን ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 13
ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት – 5
አፋር ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ – 96
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 25
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት 51
የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲ ድርጅት የመቀመጫ ብዛት – 3
ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት – 5
ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት – 1
ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 99
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 6
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 22
ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት – 1
ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት – 1
ድሬዳዋ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 189
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 47
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 189
ጋምቤላ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 156
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 14
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 149
ጋህነን ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 7
ኦሮሚያ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 537
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 171
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 513
ሲዳማ ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 190
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 19
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 190
ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት – 291
ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት – 89
ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 245
ኢዜማ ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 10
የጌዲኦ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ፓርቲ ያገኘው መቀመጫ ብዛት – 6
ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት ምርጫ ክልል ብዛት – 3
ኢዜአ