ብሔራዊ ቡድናችን ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የሚያደርገውን ጉዞ እያሳመረ ነው

March 25, 2013

 ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቦትስዋና አቻው ጋር የተጫዋተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ባደረገው ጨዋታ በርካታ የጎል ዕድሎችን መፍጠር ቢችሉም ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል።
ተጋጣሚው የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን የኋላ መስመሩን ዘግቶ በመከላከል እስከ ጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ቢቆይም ተቀይሮ የገባው ጌታነህ ከበደ በ89ኛው ደቂቃ ባሰቆጠራት ጎል ዋልያዎቹ አሸንፈው ወጥተዋል።
በዚህ መሰረትም ምድባቸውን በ7 ነጥብ ሲመሩ ትናንት መካከለኛው አፍሪካን ያሸነፈችው ደቡብ አፍሪካ በ5 ፣ መካከለኛው አፍሪካ በ3 እንዲሁም የዛሬው ተሸናፊ ቦርስዋና በ1 ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ዋልያዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ጋቮሮኒ ላይ የፊታችን ሰኔ 2 ያደርጋሉ።
አዲስ አበባ ላይ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክን 2-0፤ከሜዳው ውጪ ከደደቡብ አፍሪካ ጋር 1-1 ተለያይቶ ምድቡን በመምራት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡድንበዛሬው ጨዋታ የተደራጀ ኳስ በመጫወት ሰባት ነጥብ በመያዝ መሪነቱን መማጠናከሩ አድናቆት ተችሮታል።

Previous Story

የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ማቆም አድማው በተጨማሪ የረሃብ አድማ ጀመሩ

Next Story

የሽግግር ምክርቤት ትግሉንም ድሉንም የጋራ ለማድረግ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ድርጅቶችን ለምክክር ጉባኤ ጠራ

Go toTop