መንግሥት ልዩነቶችን በማጥበብ፣ በመቀራረብና በመመካር ሀገር የመምራት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ኢዜማ አሳሰበ

July 3, 2021
Habesha | zehabesha.infoመንግሥት ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ያሉትን ልዩነቶች በማጥበብ፣ በመቀራረብና በመመካር ሀገር የመምራት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳሰበ፡፡
በትግራይ ክልል የተፈጠረው አዲስ ሁኔታ በሀገሪቱ ሰላም፤ የፖለቲካ መረጋጋት እና አንድነት እንዲሁም በቀጠናው የወደፊት ሰላም ላይ የሚኖረውን እንድምታ መገምገሙን የጠቀሰው ኢዜማ የቢሆንስ ግምቶችን እና መውጫ መንገዳቸውንም ማስቀመጡን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ገልጿል።
ኢዜማ በመግለጫው ሀገር እየመራ ያለው መንግሥት ከሁሉ በፊት ለሀገር ሕልውና እና ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት ገልጿል፡፡
ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ፉክክር ሊኖር የሚችለው የሀገር ሕልውና ሲረጋገጥ አና የሕዝብ ደህንነት ሲጠበቅ መሆኑን አውቀው ለዚህ ዓላማ ሁሉም በጋራ እና በመቀራረብ እንዲንቀሳቀሱ ጠይቋል፡፡
መላው የሀገሪቱ ሕዝብም ይህንን እጅግ ፈታኝ ወቅት በጥበብ ለማለፍ ጥቃቅን ልዩነቶችን አስወግዶ ከምን ጊዜውም በላይ ተሳስቦ እና ተከባብሮ በአንድ እንዲቆም አሳስቧል፡፡
ሀገርን ከመበታተን ለመታደግ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የሚያደርገውን ብሔራዊ ጥሪ ተቀብሎ በመከላከያ፣ በፖሊስ እና በሌሎች የፀጥታ ተቋማት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ሀገራዊ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
በበኩሉ የሀገር እና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ባስቀደመ መልኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጨማሪ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያረጋጠው ኢዜማ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ሀገርንና ሕዝብን ከሚያስቀድሙ ማናቸውም አካላት ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል ገብቷል፡፡
EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የመረራ ጉዲና እና የዳውድ ኢብሳ ነገር (ሰማነህ ጀመረ)

Next Story

የጥሞና ጊዜ ለትግራይ ተወላጆች! – አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ 

Go toTop