መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
በ10/10/2013 ዓ/ም ሊነጋጋ ሲል ይህንን ህልም አየሁ ። ህልሙንም ሰኔ 23 ፈታሁት ። መቼም ጊዮርጊሥ ተአምረኛ አይደል ? ህልሜን ፈታው ። በእለተ ቀኑ።
ህልሙ በጣም ሥለረበሸኝ ቀደም ሲል የተረጎምኩት ፣ ከቀድሞዎቹ መሪዎች በተለየ መንገድ አገርን ለመመራት እየሞከረ ያለው የአገራችን መሪ ለይ ፣ አደጋ ሊደርሥ ይችላል በሚል መንገድ ነበር ። ህልሜና ሥጋቴንም በወቅቱ እንደማሥጠንቀቂያ ለሚመለከተው ፣ በተገቢው ድረ ገፅ ይድረሥ ብዬ ልኬዋለሁ ።…
“ይድረሥ አይድረሥ ምን አውቃለሁ
መላኩን ልኬዋለሁ ። ” ማለቴ ግን አልቀረም
በወቅቱ ትክክለኛ የህልሜን ፍቺ ያገኘሁ መሥሎኝ ነበር ። አልነበረም ። ህልሜ በሐረግ በሐረግ የሚፈታ ነበር ። ምልክቱም በወጉ መጤን ነበረበት ። ወይ የኔ ነገር ከህልሜ በፊት በማታወቁት ህልም እንድትመራመሩ አደረኳችሁ አይደል ? ይቅርታ ። ህልሜን እንሆ ፦
( እውነተኛ ህልም ነው ። ፈጠራ እንዳይመሥላችሁ )
” ዶ/ር ደብረ ፅዮን ና ሥዩም መሥፍን በነጭ ራቫ ፎር ወሥጥ ከፊትና ከሆላ ተቀምጠው መኪናቸውም ከነጭ ቪላ ፊት ለፊት ቆሞ አየሁ ። ገፃቸው ፈክቷል ።በጣም ያምራሉ ።አብሶ ስዩም መሥፍን በጣም ተውቧል ። ደብረፅዮን ደግሞ በጥቁር በተለመደው መነፅሩ አይኑ ተከልሏል። ሥዩም መሥፍን በታላቅ ዝምታ ውሥጥ ሲሆን ደብረፅዮን ባይናገርም ሰውነቱ ይንቀሳቀሳል ።
ደብረ ፅዮን ሽክ ብሎ እሥከ መነፅሩ ጋቢና በግርማ ሞገስ መቀመጡ ቢታየኝም ሹፊር ግን አይታየኝም ። በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ችሎት የሚወሰዱ ይመሥለኛል።ጠ/ሚ አብይ አህመድ በሥፍራው ነበረ ። ጠ/ሚ አብይ እነሱ መኪና ውሥጥ እንዳሉ አረጋግጦ ፣ ወደ አጃቢና ጓዶቹ ዘንድ ይሄዳል ። እኔ ምን እግር እንደጣለኝ አላውቅም እነሱ ታሥረው ከወጡበት ነጭ ቪላ ውጪ ከመኪናቸው ፊት ለፊት አድፍጬ ህንፃውን ተደግፊ በፍርሃት በነደብረፅዮን አካባቢ ያለውን ወታደራዊ እንቅሥቃሴ እያየው ነው ። ወታደሮች ከቤቱ ወጪና ውሥጥ ይንቀሳቀሳሉ ። አንድ ወታደርን ደብረፅዮን በጥቅሻ ጠርቶት የኤትኤም ካርድ የመሰለ ቢጫ ነገር ደብቆ ይሰጠዋል ። የዚን ጊዜ እጅግ በመሥጋቴ እየጮኹ ወደነ ጠ/ሚ አብይ እሮጣለሁ ። ወዲያው ተኩሥ ይቀልጣል ። ብዙ ሰው ይሞታል ። ብዙ ወታደሮችም ጠ/ሚ አብይ ከአደጋው ለመከለል ዙርያውን ከበው አብዛኞቹ ተረባርበው ከጥፋቱ ይጋርዱታል ። ከአፍታ በኋላ በወታደሮች መሐል ሲንጓራደድ አየዋለሁ ። አብይ ይተርፋል ። በዛ ቀውጢ ሰዓት ቦንብ ፣ ቦንብ ብዬ እጮኸለሁ። እዛ የተገኘ የወታደሮቹ ሻንጣ ሳይቀር ይበረበራል ። በአንድ ሻንጣ ውሥጥም ፣ ድምፅ የሚያሰማ በሰዓት የሚፈነዳ ፈንጂ ይገኛል ። የፈንጂ ኤክሥፐርትም እንዲያወጣው ይታዛዛል ። “
ለመሆኑ ነጭ ራቫ ፎር ና ነጭ ቪላ በምን ይመሰላል ? በጣም ማማር ፍቺው ምንድነው ። የሥዩም መሥፍን ዝምታ በሞት ይመሰል እንበል ፣ የደብረፅዮን እንቅሥቃሴ እና ቢጫ የኤቲ ኤም የምትመሥል ካርድ ምንድናት ? ( አለመሞቱን ያመለክታል ። ) ለምን በዛ ነጭ የተዋበ ህንፃ ግርግዳ ጥግ እኔ ተገኘው ? (ምናልባት ለዓመታትት በፃፍኳቸው የዛሬ ሰው የነገ ሬሣነታችንን በሚያሥገነዝቡ ፅሁፎቼ ና የወቅቱን የትግራይን ጉዳይ በማሥመልከት ፣ በፅሑፎቼ ውሥጥ በጠቆምኳቸው ማሥጠንቀቂያዎች ይሆንን ? ) እርግጥ ሞት ለሁሉም ሰው በተራ የሚደርስ ነው ። በምድር ላይ ለዘላለም የሚኖር ከቶም የለም ። ሁሉም ሰው ወደ አፈርነት መቀየሩ አይቀርም ። በማንኛውም የሞት መንገድ ህይወቱ ይለፍ ፤ ሰው አሥቀድሞ አፈር በመሆኑ ወደአፈር መመለሱ አይቀርም ። ( ልብ በሉ ከልጅነት እሥከ እውቀት የአፈርን ምርት በልተን ነው ዛሬ ጎልማሳና ሽማግሌ የሆን ነው ። ) ፤ ሰው ሁላ አላፊና ጠፊ ነው ። ማንም ዘላለማዊ አይደለም ። …በዚህ እውነት ዙሪያም የሚያጠነጥኑ ፅሑፎች ደጋግሜ ፅፊያለሁ ።… ለዚህ ይሆን ከነጩ ቪላ ጥግ የነጮቹን ሤራ ተገንዝቤ ፣ በፍርሐት አድፍጬ የተገኘሁት ?
በነገራችን ላይ ፤ ሲአይ ኤ ኢትዮጵያን ለመጋጥ እንዲህ ያሰፈሰፈ ጂብ ሆኖ በቅርብ በገሃድ ይታያል ብዬ ባላሥብም፣ የምእራቡን እና የተባበረችውን አሜሪካ የሚዘውሯት ቱጃሮች ለኸጫቸውን እያዝረበረቡ ለዘመናት ኢትዮጵያን በመጎምጀት እንደሚያዮት ና ኢትዮጵያም የምትጠፋው በራሷ ዜጎች እንደሆነ ገብቷቸው ያለመታከት ሤራቸውን ለመተግበር ሲሰሩ እንደነበር ግን ህሊና ያለን እና ከነጮቹ የተሻለ አእምሮ ያለን እኛ ኢትዮጵያዊያን እናውቅ ነበር ።
ወደህልሜ ልመልሳችሁ ፦
ወታደሩ በምን ይመሰላል ? በሻንጣ ውሥጥ ያለው ፈንጂሥ ?
ህልሜን ዛሬ ላይ ሆኜ ለመፍታት እችላለሁ ። ፈንጂው ወይም ታይም ቦንቡ ፣ኢትዮጵያን ለማጥፋት በባንዳነት ከታሪካዊ ጠላቶቻችንን እና በሰው ደም ወይም በአፍሪካውያን ደም ከደለቡት ጅብ ምእራባውያን ቱጃሮች ጋር የወገነውን ህወሓትን የሚመለከት ነው ።
ዛሬ ለጊዜው ከፊሉ የትግራይ ከተሜ ከአሸባሪው ህውሃት ጋር ቢወግንም ፣ ነገ ከነገወዲያ የለ ኢትዮጵያ ህልውና እንደሌለው ሲረዳ ኢትዮጵያ ማሪኝ ማለቱ አይቀርም ። ወዳጄ ላሚቷን ጠልተህ ወተቶን መመኘት ጅልነት መሆኑንን እወቅ ። የኢትዮጵያ መንግሥት በህግ አግባብ በሚመረጥ የትግራይ ከፍለ ሀገር ( በኢፈዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ) አሥተዳደር ጋር ይተባበራል እንጂ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ያደርገዋል ብሎ ማሰብ በራሱ ይከብዳል ።
አንድ ፣ አንድ ሊሂቃን ፣ የነበረው እንዳልነበረ ሆኗል ። አብቅቷል ። ይሉናል ። ሆኖም ” ግራ የተጋባው ፤ ከሁለቱም ጎን ያልቆመው የትግራይ ህዝብ የማሰቢያ ጊዜ ይሰጠው ፤ ለአምሥት ና ለስድስት ወር ከጦርነት እፎይ ይበል ። ” አለ እንጂ ፣ ማዓከላዊ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጁት የጥፋት ኃይሎች ወደ ሥልጣን ይምጡ አላለም ። የትግራይ ህዝብ የራሴ ጅብ ይብላኝ የሚል የዋህ እንደማይሆን እና ለዘላቂ ጥቅሙ ብቻ ሳይሆን በደም ከተሳሰረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላለመለየት ፣ ህውሃቶችን “በቃችሁ ! ” እንደሚል አሥባለሁ ።
ህውሃት በባንዳነት አገር የምትጠፋበት ቦንብ ዛሬ ና አሁን በአገር ላይ ማንጠልጠሉን ፣ የትግራይ ህዝብ አሥተውሎ “ይህ የቅጥረኝነት ጨዋታ ይበቃል ! ” በማለት ፣ ወደ ህሊናው ሲመለስ ነውና ፤ ላሚቱን ከፊት ለፊቱ ዞር ማድረግ ተገቢ ነው ። የትግራይ ህዝብ በንፁህ ህሊና የራሱን መሪ እሥከሚመርጥበት ጊዜ ድረሥም በጀት እና መሠረተ ልማት አይኖረም ። ምናልባት ቢኖር ለአሸባሪው የወንድ በር መሥጠት ነው ። በጀት መሥጠት ብሎ ነገር ግን አይኖርም ።
ህውሃት የሸሸጋትን በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የተሰራች ፣ በጊዜ የምትፈነዳ ቦንብ መቼ ና የት እንደምትፈነዳ አይታወቅም ና ከዚህ ፀረ _ ኢትዮጵያ ኃይል ጋር ድርድር አይሰፈልግም ። ትግራይ የኢትዮጵያ ታሪክ ናት ። ቅኝ ገዢዎች ካቋቋሙት የእብዶች ሥብሥብ ጋር ድርድር ከቶም አያሥፈልግም ። ህውሃት እኮ በቢላ ህዝብን እያሥፈራራ የሚገዛ ሂትለራዊ ሤጣናዊ ኃይል ነው ። ከአልቃይዳም ሆነ ከአቦኩሃራም በመቶ እጅ የሚበልጥ ጨካኝና ግፈኛ ነው ።
ከአሸባሪ ቡድን ጋራ ፣ ድርድር ይቅርና ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ እውቅናውና ፣ ግልፅ ቁጥጥሩ ፤ በአየር የሚደረግ እርዳታን መፍቀድ አይኖርበትም ። …ገለልተኛ የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ሊቋቋም ግን ይቻላል ።
ማጠቃለያ
ህልሜ ዛሬ ተፈቷል ። የነጩ ቪላ ሚሥጥር የነጮች ረዢም እጅ ነው ። ነጮቹ ትላንትም በኢትዮጵያ ጉዳይ እጃቸው ነበረ ። ዛሬም አለ ። ለልማት ና ለብልፅግና በተነሳን ቁጥር ለጥቅማቸው ሲሉ እርሥ በእርሥ የሚያባሉን ዛሬም የአፍሪካ ቅኝ ገዢነበሩት ናቸው ።
የግንጠላ ጥያቄ ከትግራይ ህዝብ ከቶም አይነሳም ። የማንን ወተት ጠጥቶ ሊኖር ነው ፣ እገነጠላለሁ የሚለው ? ያሳደገችውን ኢትዮጵያ ፣ የምንጅላቶቹን ሀገር “አልፈልግሺም ። ከአንቺ ተለይቼ እኖራለሁ ። ” ማለት ይቅርና በህልሙም ፣ የሚያስብው አይመሥለኝም ።
ህዝብ ሥንል ከ10 እና ከ11 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ መካከል ፣ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን የዘረፋው ጠበል የደረሰው ከህውሃት ጋር የቆመው ብቻ ነው ፤ ካልን ተሳስተናል ። የትግራይን ህዝብ በሙሉ በፀረ ኢትዮጵያዊነት መፈረጅ ትልቅ ሥህተት ነው ። ተመሳሳይ ችግር በአዳዋ ጦርነት ታይቷል ። በ1928 በማጨው ጦርነት ከዚህ የከፋ ባንዳነት ታይቷል ።ትግራይን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለይቶ ማየት ና ለግንጠላ ድርድር ማቅረብ ለቅኝ ገዢዎቻችን ሃሳብ መንበርከክ ነው ።
እናም የትግራይ ህዝብ የተጎነጎነበትን ሤራ በቅጡ ለመረዳት እድሉ ይሰጠው ። መኩራት ያለበት በኢትዮጵያዊነቱ እንደሆነ ያምናል ። በተጣበቀ አንጀቱ በዶላር የጠገቡትን ባንዳዎቹን ምሥኪኑ የትግራይ ህዝብ የሚደግፋቸው አይመሥለኝም ።የሚቀምሰው የቸገረው ፣ብዙሃኑ ህዝብ በሃሺሽ በሠከሩ አራጆች ተከቦ በፍርሃት ቆፈን ውሥጥ ነው ፤ የሚኖረው ። የእናቱን የኢትዮጵያን ወተት እንዳይጠጣ የከለከሉትም በሥሙ የሚነግዱ ሃሺሽ ያሠከራቸው ባንዳዎች መሆኑንን አሣምሮ ያውቃል ።
የህልሜ ፍፃሜ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳው ቦንብ ፣ ይከሽፍ ዘንድ ፣ ለፈንጂ አክሻፊ ባለሙያ መሠጠቱን ያመለክታል ። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር ለጊዜው ከመቀሌ መውጣቱን ና አጥፊ የሆነውን ፈንጂ ማክሸፉን ግልፅ አድርጎልኛል ። የታቀደው የኢትዮጵያን ጦር የማጠልሸት ሤራ ከሽፏል ። ዕቀባውና ጦር ማሥገባቱም እንዲሁ ። በህዝቡ መሐል ህውሃቶች ተሸሽገው ከጀርባው ተኩሰው በዘግናኝ ሁኔታ ጦሩን የገደሉትና ከኃይሉ ቆርጠው ምርኮኛ ያደረጉት በወገኑ ላይ ጥይት ባለመተኮሱ ነው ። ሠራዊቱ ባልተገባ መሰዋትነት ህዝቤን አልገልም ብሎ ሞቷ
። በመሰዋትነቱም ኢትዮጵያን አድኗል ። የትግራይ ኃይማኖተኛ ህዝብም ይህንን ይገነዘባል ።በቅርብ ቀንም አሸባሪውን ህውሃት ህዝቡ በእኛ መነገዱ “ይበቃል ! “እንደሚለው ተስፋ አደርጋለሁ