የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሽብር ሰሞኑን 14 የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች ከተገደሉ በኋላ ዛሬ በሺህ የሚቆጠሩ ከ እርሻ ማሳቸው ተባረዉ ከተማ መጠለላቸዉን ቪኦኤ አማርኛ ዘግብዋል።
ይህ ላለፉት ሁለት ዐመታት ያላባራው ጥቃት ዋናዐላማው የአማራን ተወላጆች ለማባረር በወያኔ ኦነግ በክልሉ ታጣቂዎች የታገዘ ዘር ፅዳት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወያኔና ኦነግ በመሀከላቸው ከደጅ የጋራ ሠንደቅ ትብብር ዉጭ በሀገር ቤት የሚያደርጉት የመሬት ቅሚያ ነው ልክ ሰሞኑን ኦሮሞ ከተማዎች ያየነው አማርኛ ተናጋሪና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ላይ እንዳነጣጠረው ግድያና ሀብት ቃጠሎና ዝርፊያ።
OMN የጉሙዝ ማህበረሰብ ተጨፈጨፈ ጩኸት ባለፈውየሰማነው አማራዉን ከሌሎች ጋር በማጋጨት የሚፈልጉትን መሬት የመቆጣጠር ዕንቅስቃሴ ከወያኔ የቀድሞ የክልሉ ሸሪኮች ጋር የማስፈፀም ትግል ነው።
የዳዊትመኮንን የ አሶሳ ተልዕኮ ከ ጃዋር OMN ተልዕኮ ጋር የሚናበብ መሆኑን ለመገንዘብ የፖለቲካ ተንታኝ መሆንን አይጠይቅም።
ኅዳሴ ግድቡ አካባቢ በመፈፀም ላይ ያለውን ጥቃት የክልሉ አፍቃሪ ወያኔ ኦነግ ታጣቂዎች አላየንም አልሰማንም ብቻ ሳይሆን ከጀርባው መኖራቸው አያጠራጥርም።
ኅዳሤ ግድቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነው ሌሎቻችሁ አያገባችሁም የሚለው ካርታ የትግራይን ክልል ከቤሻንጉል ጉሙዝ አገናኝተው በድንገት የለቀቁትን ማስታወስ ተገቢ ይሆናል። አሁን የቀረው የወያኔ ጦር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጥሪ አድርጎልኝ ገባሁ ማለት ብቻ ይሆናል።
የወያኔ ሹማምንት እኛን በሌላው ክልል ችግር አትጨምሩን ተጠያቂው ብልፅግና ሲሉ ይደመጣሉ። አዎ ልክ እንደ ኦሮሞ ክልል ብልፅግና ህዝቡን ቛሞ እንዳስፈጀው የቤኒሻንጉል ክልል ብልፅግናም በተራው እያስፈጀ ነው።
የአማራውን ማህበረሰብ ከሚኖርበት ማፈናቀል ወያኔ የጀመረው የዛሬ 29 አመት ሲሆን እነዚህ አፈናቃዮች ከዛሬ ሁለት ዐመት በፊት ጀምሮ በበላይነት ኦነግ ሲመራ ወያኔ በገንዘብ ና በክልሎች መዋቅሩ ከመቀሌ እያስተባበረ ይገኛል።
በዛሬው ቪኦኤ አማርኛ ጥቃት የደረሰባቸው እነማን ከመከላከያ አማራዉን እያባረሩ እርሻዉን እያቃጠሉ መሆናቸዉን በግልፅ መስክረዋል።
መከላከያው ከወያኔና ኦነግ ጠርቶ የክልሎችን ደህንነት እስኪያስጠብቅ የአማራ ገበሬዎች በሠላም ማረስ ነጋዴዎች መነገድ ተማሪዎች መማር አማኞች በሠላም መፀለይ ይቸገራሉ።
እራሳቸዉን ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፓርቲዎች ይህን መከራዉን የሚያይ ህዝብ ጎን መቸ ይሆን እቦታው ሄደው አለን የሚሉት ???
https://youtu.be/nIs2ypqOHh8