ዉይይት፣ ኢትዮጵያ ከእንግዲሕ

July 21, 2020

ከድምፃዊነቱ እኩል በ2010 ለተደረገዉ ለዉጥ በተደረገዉ ትግል እዉቅናን ያገኘዉ ሐጫሉ ሁንዴሳ  ባለፈዉ ሰኔ 22 መገደሉና መዘዙ ያስከተለዉ ቁጣ፣ ጥፋትና ዉዝግብ ለዓለም ደግሞ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያበቃዉ ለዉጥ ጨርሶ እንዳይጨናጎል ብዙዎችን እያሰጋ ነዉ

ማስታወሻ፤- ይሕ ዥግጅት ባለፈዉ ዕሁድ (12.11.2012) የተሰራጨዉ ዝግጅት ረጅም አካል ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በየዘመኑ በተለይም ባለፉት 80 ዓመታት የተደረጉት የሥርዓት ለዉጦች ለየዘመኑ ሕዝብ የተሻለ አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ የዕድገት ብልፅግና ተስፋ እየፈነጠቁ በየዘመኑ ሥልጣን በሚይዙት ኃይላት ፍላጎትና በልሒቃን ስሕተት ተጨፍልቀዋል።

ኢትዮጵያዉን አርበኞች የኢጣሊያን ወራሪ ጦር ከ5 ዓመታት ትግል በኋላ በ1933 ድል አድርገዉ ሐገራቸዉን ነፃ ማዉጣታቸዉ፣ ለዚያ ዘመኑ ትዉልድ የጀግነቱ ኩራት፣ነፃ የመዉጣቱ ብስራት፣በነፃ ሐገሩ እኩል የመኖር-የመጠቀሙ ተስፋ፣ የዕድገት ፍላጎቱ መሰረት መጣሉ መስሎ ነበር።

የ1966ቱ የሥርዓት ለዉጥ የብዙ ኢትዮጵያዉን የረጅም ጊዜ ትግል ዉጤት፣ የልማት ዕድገት፣የእኩልነት ተስፋም ነበር።በ1983 ሌላ የሥርዓት ለዉጥ ነበር።ሌላ ተስፋ።የሰላም፣ የዴሞክራሲ፣ የልማት፣ ብልፅግና ትልቅ ተስፋ።

መጋቢት 2010 የበረቀዉ የለዉጥ ጭላጭልም እንዲሁ አዲስ ብሩሕ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር።ሁሉም ለዉጥ ግን ሕዝብ የሚመኘዉን ወይም ለአብዛኛዉ ህዝብ የሚጠቅመዉን ልማት፣ዕድገት፣ መልካም አስተዳደር አላመጣም።

ከድምፃዊነቱ እኩል በ2010 ለተደረገዉ ለዉጥ በተደረገዉ ትግል እዉቅናን ያገኘዉ ሐጫሉ ሁንዴሳ  ባለፈዉ ሰኔ 22 መገደሉና መዘዙ ያስከተለዉ ቁጣ፣ ጥፋትና ዉዝግብ ለዓለም ደግሞ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ያበቃዉ ለዉጥ ጨርሶ እንዳይጨናጎል ብዙዎችን እያሰጋ ነዉ።የስጋቱ ደረጃ የልሒቃኑ ልዩነት  እና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ጉዞ ያፍታ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የሕብር ሬዲዮ ሐምሌ 13/14 ቀን 2012 ዓ.ም. ፕሮግራም

Next Story

የሁለቱ ሰልፎች ወግ – ሰሎሞን ጌጡ ከኑረምበርግ

Go toTop