ይድረስ ለሚመለከትህ ( እኔን ጨምሮ ) (ዘ-ጌርሣም)

July 3, 2020

አዕምሮህ በትቢት ተወጥሮ
ልብህ በቅናት ነፍሮ
እንባህ ጥላቻን ያበቀለ
የቀረበውን አርቆ የወረደውን የሰቀለ
ህዝብን ክህዝብ እያጣላህ
የአሉባልታ ወሬ እያስፋፋህ
የሰላምን ተስፋ ያጨለምክ
የዕድገትና የሰላም ችግኝ የነቀልክ
የግል ኑሮህ አልሳካ ቢል
አገር ትጥፋ ህዝብም ይለቅ የምትል
ይድረስ ለሚመለከትህ
ይህ ከሆነ ገፀ ባህሪህ
ቀናተኛ የማትሠራ
ቀኑ የከዳህ ስታወራ
የድሃ ጉሮሮ አናቂ
የወሬ ቋት አሳባቂ
ከሞቀበት አዳናቂ
የኔ የምትለው የሌለህ
የአዕምሮ ድሃ የሆንህ
ይድረስ ለሚመለከትህ
ይህ ከሆነ ገፀ ባህሪህ
ለከርሳሙ ሆድህ ብለህ
ሰብዕናህን ለንዋይ ሽጠህ
የውርደት ሸማን ተላብሰህ
አባ ዳኘው ሞት ሲጠራህ
የት ይሆን ያኔ መግቢያህ
ይድረስ ለሚመለከትህ
ይህ ከሆነ ገፀ ባህሪህ
ሙሉ እንጀራ አስጠልቶህ
ፍርፋሪ የሚያስምኝህ
የራስህን ሆድ አብልጠህ
የማታስብ ለልጆችህ
በአኩይ ዓላማ ደንዝዘህ
ትቀራለህ ከንቱ ሁነህ
ይድረስ ለሚመለከትህ
ይህ ከሆነ ገፀ ባህሪህ
የኢትዮጵያ አምላክ ተፋርዶ
ሳትሞት በቁምህ አዋርዶ
የሞት ሞትን አስጎንጭቶ
ከጌቶችህ ጋር አጋጭቶ
በህሊና ፀፀት ገርፎ
የሠራ አካላትክን አርግፎ
በቁምህ ፍዳ ያስከፍልህ
የከሰረና ብኩን ያርግህ
ተማርኩ ብለህ የደነቆርክ
በትዕቢት የተወጠርክ
የኢትዮጵያን ሞት የተመኘህ
ዜሮ ራስህ ባዶ ያርግህ
የወለድከውን አያስምህ
የዘራኸውን አያስቅምህ
ዜሮ እንደሆንክ ዜሮ ያርግህ
ይድረስ ለሚመለከትህ
ይህ ከሆነ ገፀ ባህሪህ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአባቶች ምክር – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን

Next Story

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የዛሬው ንግግር

Go toTop