በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። የታላቋ ደብራችን የሚኒያፖሊስ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመጪው ታህሳስ 6 2006ዓ.ም/ ዲሴምበር 15 2013 ዓ.ም አጠቃላይ የምእመናን ጉባዔ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗ በአስተዳደር ቦርዱ/ሰበካ ጉባዔው መገለጹ ይታወቃል። በዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ በመገኘት የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ዘላቂ ሰላም በተመለከተ የማያዳግም ውሳኔ በመስጠት ሁላችንም ለቤተክርስቲያናችን እድገት በአንድ ልብ ሆነን የምንሰለፍበትን ሁኔታ ለመመካከር ይቻል ዘንድ የቤተክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል የምንል ምእመናን ሁሉ ታኅሳስ 5 2006ዓ.ም/ዲሴምበር 14 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት/1፡00pm East Phillips Business Unit 2307 17th Ave. S. Minneapolis, MN 55404 እንድንገኝ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
ለሰላምና ለአንድነት ከቆሙ ምእመናን ተወካዮች።