የሩዋንዳ ኤምባሲ ጥበቃ የሆኑት አቶ ሸረፋ በጥበቃ ላይ እንዳሉ በተተኮሰ ጥይት ሞተዋል። የኤምባሲው የሴኩሪቲ ኃላፊ ሚስተር ጆን በነበረው ሁኔታ በማዘንና በመበሳጨት “እንዴት በስራ ላይ ያለን ሰው ተኩሳችሁ ትገላላችሁ? ኤምባሲውን ደፍራችኃል” በማለት ፖሊሶች ወደ ግቢው እንዳይገቡ ያደረገ ሲሆን የሟችን ሬሳ ከሌሊቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ድረስ ሳይነሳ ቆይቷል። በድናቸው ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።
በአሁኑ ወቅትም አባዲና ቦታው ላይ መጥቶ ምርመራ እያከናወነ ይገኛል። የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በብዛት ቦታው ላይ ይገኛሉ።
ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ