“ቅዳሴ” ፣በኦሮምኛ ፣ “አዛን” በትግሪኛ ፣ በመላው ኢትዮጵያ መሥጊዶች ና  ቤተክርስቲያናት አሁኑኑ!!!” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

September 3, 2019
 ”   “ቅዳሴ” ፣በኦሮምኛ ፣ “አዛን” በትግሪኛ ፣ በመላው ኢትዮጵያ መሥጊዶች ና  ቤተክርስቲያናት አሁኑኑ!!!”
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
 መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው። ሰሞነኛው ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሰጠ የማበጣበጥ የቤት ሥራ ነው።ሰዎች ዝም ብለው የፈጣሪን ሥራ እያሥተዋሉ በመንገዱ መጎዝ ሲገባቸው ፣ ፈጣሪን አቅመ ቢሥና  በቋንቋቸው ካለመኑት የማይሰማ አድርገውታል።ሩሲያ ፣ግብፅ ፣ ግሪክ፣እየሩሳሌም  የኦርቶዶክስ ቤተክርስቴያን አለች ።ብዙ ቋንቋዎች አሉ።ግን የሚቀደሰው በጥንቱ መንገድ ነው።
   ግእዝ ና አማርኛ   ከአማራ ጋር ብቻ የተያያዘ የመሰላቸው ያለአዋቂዎች  የእርጎ ዝንብ ባይሆኑ ደሥ ይለኛል ። ይህ የማበጣበጥ ሥራ በማን እስፖንሰርነት ነው የሚካሄደው ብሎ ምእመኑ እንዲያሥብ ያደርገዋል ና ከዚህ እሳት የመጫር ተልኮ ቢታቀቡ መልካም ነው። ዓፄ ዮሐንስ ዝም ብለው አንገታቸውን ለደርቡሽ ጦር አላሥቆረጡም። ጭንቅላታቸውም እንደባንዲራ ተሰቅሎ በሱዳን ከተማ አልተዘፈነበትም
   የእሥከዛሬ መስዋትነት ና ድል ፣ አሻራ በኦርቶዶክሳውያኑ ግንባር ቀደም ተሳትፎ እንደመጣ ታሪክ ይመሰክራል።እርግጥ ነው፣ የመንግሥታት ራእይ ና ውድቀትም ቤተክርስቲያኖን ከመናቅ የተነሳ ተከሥቷል።
       ዓፄ ቴዎድሮሥ የእምነትን ኃይልን ዘንግተው፣ህዝብ ከጎናቸው እንዳይቆም አድርገዋል። ቅንነትም ሆነ ጀግንነት ሚዛኑን የጠበቀ ና በፈጣሪ የእውነት ና የትዕግሥት ባለቤትነት ካልታጀበ ከንቱ ነው።
     ዶሮ ጭራ፣ጭራ መታረጃዋን እንዳወጣችው ይሆናል ፍፃሜው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመንም ሆነ በትልልቅ ከተሞች ያለ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሳይቀር፣ለቋንቋ ና ለነገድ ግድ የለውም። ማንኛውም ክርስቲያን ሰው መሆኑን እና ሰውንም የሚያውቀው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው። እናም ሁሉም አማኝ ወንድም ና እህቱ ነው።
     እናም በቋንቋ ልንሟገት ና የራሳችን አንጡረ ሀብት የሆነውን ግእዝ ፣ ለማጥፋት መጣር እና ቅዳሴ በኦሮምኛ ቋንቋ ይሁን ማለት አግባብ አይደለም።
   ይህ ማለት እኮ “ቅዳሴ” ፣በኦሮምኛ ፣ “አዛን” በትግሪኛ ፣ በመላው ኢትዮጵያ መሥጊዶች ና  ቤተክርስቲያናት ለምን አሁኑኑ አይካሄድም? ማለት ኑው።
    ነገ ተነገወዲያ ደግሞ፣ “በክልልችን በትግሪኛ አዛን መደረግ አለበት፣በኦሮምኛም መቀደሥ ያለበት በሁሉም ቤተክርስቲያን  ነው።ሁሉም ነገዶች በቋንቋቸው በቀን አምስት ጊዜ ፣   “አዛን” ማደረግ አለባቸው።በየክልሉ ያሉ አብየተ ክርስትያነት በሙሉ የየክልሉ ንብረት ናቸው። ቅዳሴም በየክልሎቹ  ቋንቋ መካሄድ አለበት እንጂ ለምን በኦሮምኛ  ብቻ እንዲከናወን   ይጠየቃል?…” ማለታቸው አይቀርም። ይህ ከሆነ ደግሞ እድገት ና ብልፅግናችንን የማይፈልጉ እልል በቅምጤ ! “ይላሉ።
  (…)
   እንግዲህ  ተጋፊ ወይም ድንበር ዘለል  ፖለቲካ ይሉሃል ይሄ ነው።ዓለማዊው ፖለቲካ፣ዓለምን መበጥበጥ አልበቃ ብሎት በመሰሪ ሰው እየታገዘ  መንፈሳዊውን ዓለም ይበጠብጣል።ከላይ የተጠቀሰውንም ጥያቄ ያሥነሳል።
      መሰሪው ሰው ፣የሃይማኖተኛውን እምነት የሚገዳደር ፣ ቆሻሻ  ሃሳብ አመንጭቶ ፣ከንፁህ የእምነት ክንውን ጋር በመደባለቅ  ይፈተፍታል።ለዘመናት የቆየን የእምነት ክንውን ካላጠፋሁ ሞቼ እገኛለሁ ይላል።
   በመሠረቱ ይህ ሰው ያልበላውን ነው የሚያከው።  ያልበላውን በማከክም አያባራም። ሌሎች እንዲበላቸው ያደርጋል።ሌሎች እጅግ በልቷቸው  ሲያኩም  ” ሠራሁላቸው ! ”  ብሎ ይስቃል። “ደም ይሳቅና !” ቀና አሣቢ መሥሎ የመከፋፈል መርዙን ረጭቶ ሲያበቃ ዞር ብሎ ይሳቅብን???
(…)
   እንዲህ ዓይነቱ አደገኛ የጠብ ሣይሆን እርስ በእርስ የሚያጫርስ ና የመስቀል ጦርነት የሚያሥነሣ ጥያቄ ኃላፊነት የጎደላቸው ብቻ ሣይሆኑ ፣ በገንዘብ የተገዙ ሰዎች፣  የሚያነሱት እንጂ በቅንነት የተጠየቀ  ጥያቄ አይደለም።
     ቅንነት የጎደለው መሆኑ እና ዓለማዊነቱ የሚገለፀው መንፈሳዊውን ዓለም በመገዳደሩ ና እግዛብሔር ለቋንቋ ና ለነገድ እንደማይገደው ያላወቀ በመሆኑ ነው።ይህም ብቻ አይደለም ይህ ሰው ፈጣሪን እንደሰው ቆጥሮታል። ማንም ሰው የፈለገውን ኃይማኖት መምረጥ ይችላል።ወይም በራሱ ሌላ ሥያሜ ሰጥቶ ኃይማኖት መፍጠር ይችላል።በዓለም እስከ ሃያሺ የሚደርስ ኃይማኖት ተፈጥሯል።
    ማንኛውም መሠሪ ሰው የራሱን እና የመሰሎቹን ኃይማኖት ፈጥሮ ከፈጣሪው ጋር በመንፈስ መነጋገር መብቱ ነው።ይህንን እውነትም የሚያጣው አይመሥለኝም።
   የሱ ዓላማ ሌላ ነው።ዓላማው  ኢትዮጵያውያንን በኃይማኖት መከፋፈል ነው።ቀዳሚ የልማት፣ የዴሞክራሲ ና የፖለቲካ ጥያቅያቸውን ማዘናገት ነው።እንደ ሰው ሳይሆን አእምሮ  እንደሌላቸው እንደሚጠፉ እንሥሣት እንዲነካከሱ ነው የመሰሪው ሰው ዓላማ።
   የመሰሪው ሰው ዓላማ ይህም ብቻ አይደለም።ለም እና አየሯ ምግብ የሆነውን ሀገራችንን     በኃይማኖት ፣በቋንቋ፣ እና በፖለቲካ ልዩነት ሰበብ የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ መክተት ነው።
    ህዝቡን እርስ በእርሱ እንዲነታረክ በማድረግ፣  ከአንድነቱ ይልቅ ልዩነቱን በማጉላት እና ሰውነቱን በማሥረሳት ፣ካራ እንዲማዘዝ ነፍጥ እንዲያነሳ በማድረግ ፣የጋራ ተጠቃሚ ከሚያደርገው  የጋራ ልማት እንዲያፈገፍግ ማድረግ ነው።ይህንን በማድረግም ብድራታቸውን ከጌቶቻቸው ይቀበላሉ።
     ሰው እንዴት በገንዘብ ኃይማኖትን ለማፍረሥ ይነሣል?
ያሳፍራል።

Previous Story

የፈተናው ዘርፈ ብዙና ከባድ ነው – ጠገናው ጎሹ

Next Story

የኦሮምያ ቤተ ክህነት፡- ለትክክለኛ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ – ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Go toTop