ትግራይን መገንጠል ያስፈልጋል? – ማሕበር ኢትዮጵያውያን ተጋሩ

July 4, 2019

በኣሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከኣካባቢ ኣሰተዳደር ጥያቄ ያለፈ የመገንጠል ጥያቄ ዓላማ ለመተግበር የሚታገል ቡድን የለም። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ የኣንድነት መንፈስ ስለሚያመለክት ተገቢ ትኩረት ሊሰጠውና ሊዳብር ይገባዋል። ከዚህ ኣንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ በመበታተን ኣፋፍ ላይ የምትገኝ የሚያስመስል ከእውነት የራቀ ቅስቀሳ ቦታ ሊኖረው ኣይገባም።

በትግራይ ውስጥም የመገንጠል ዓላማ ይዞ የሚታገል ቡድን ባይኖርም ደብረፅዮን (ዶ/ር) በትግራይ ህዝብ የመገንጠል ዝንባሌ እንደተከሰተ ገልፀዋል። ገለጻው ልክ መሆኑን በተጨባጭ ለማሳየት ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጋሉ። በኣንድ በኩል የህዝብን ፍላጎት ለማወቅ የሚያስችል ህዝቡን የመጠየቅ ድርጊት (ሰርቨይ) እና ድርጊቱን የሚፈጽም ሞያዊ ተቋም፡ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብ ነጻነት ያስፈልጋሉ። ትግራይ ውስጥ ሰላም ሊያስከብር፣ ሲፈልግም የወጣቶች መንጋ ሊያሰማራ የሚችል የክልል መንግስት

ኣለ የተጠቀሱት ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ግን የሉም። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ነ ነት ተሰምቶት በመንግስት የማይፈለግ ፍላጎቱን ሊገልጽ ኣይችልም።

የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ባይሙዋሉም የተወሰኑ የትግራይ ምሁራን የኢትዮጵያ ኣንድነት ኣስፈላጊነትን ማጣጣል ጀምረዋል። ይህ የመገንጠል ዝንባሌ በጥቂት የህወሓት መስራቾች የተጀመረ ነው። ምሁራን ፍላጎታቸውን የማስራጨት ኣቅም ስላላችው ዝንባሌው ክህወሓት ጋር ይሁን ካለ ህወሓት ሊቀጥል ስለሚችል በቀላሉ የሚታይ ኣይደለም።

በዚህ መሰረት የመገንጠል ዝንባሌው ምንጭና ምክንያቶች ማወቅ ያስፈልጋል። በ68 በተጻፈው የህወሓት ማኒፌስቶ ትግራይን መገንጠል እንደ ዓላማ ተገልጾ ነበር፣ የማኒፌስቶው መገንጠልን የሚመለከተው ይዘት የጥቂት ሰዎች ፍላጎት እንጂ የድርጅቱ ኣባሎች የተስማሙበት ስላልነበረና ተቀባይነት ስላልነበረው በትጥቅ ትግሉ ጊዜ እንደ ኣጀንዳ ተነስቶ ኣያውቅም። ሆኖም የመገንጠል ዓላማ ያነገቡ ሰዎችም ማንነታችው በድርጅቱ ኣባሎች ሳይታወቅና ከስልጣን ሳይወርዱ ቀጥለዋል።

ህወሓት መንግስታዊ ስልጣን ከያዘ በ ላም የመገንጠል ዓላማ የጻፉ ሰዎች በይፋ የመገንጠል ፍላጎታቸውን ባይገልጹም ሌሎች ሰዎች ታሪክን ለታሪክነቱ ሳይሆን ለፖለቲካዊ የጥላቻ ቅስቀሳ እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታ በመፍጠራችው በትግራይ ህዝብ ባልተለምደ ሁኔታ መገንጠል የተወሰኑ ምሁራን ኣጀንዳ ሆነዋል። የመገንጠል ኣጀንዳው እየጎላ የመጣው የህወሓት ኣመራር በኢትዮጵያ ደረጃ የበላይነቱን ካጣ ወዲህ ቢሆንም ህወሓት በኢትዮጵያ ደረጃ የነበረውን ስልጣን ለማስመለስ የሚያደርገው ቅስቀሳ እንደሆነ ማየቱ ትክክል ኣይመስልም፤ ምክንያቱም የበላይነቱ በትግራይ ህዝብ ላይ ያስከተለው ችግር የትግራይ መሰረቱን እንደሚያሳጣው ያውቃል።

የመገንጠል ቅስቀሳውን የሚያቀጣጥሉት ዋና ምክንያቶች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ህዝቡን የመደምሰስ ይፋዊ ኣረመኔዊ ቅስቀሳዎች ናቸው። የትግራይ ተወላጆች ከሌሎች ክልሎች፡ በተለይ ከኣማራ ክልል መፈናቀላቸው፣ መገደላቸው፣ ከትግራይ ጋር የሚያገናኘው መንገድ መዘጋቱ፣ በመንገድ ላይ የሚፈጸሙት ዝርፊያዎች ወዘተ.. በተራውና ባላጠፋ ህዝብ ላይ የሚደርሱ ችግሮች ስለሆኑ የመራራቅ ስሜት ፈጥርዋል፣ ድርጊቶቹ ህወሓትን የሚያጥናክሩ እንጂ የሚያዳክሙ ኣይደሉም።

ኢትዮጵያ ታሪካዊት ኣገር ናት፣ ህዝ  ም በብዙ መንገድ የተሳሰረና የተቀላቀለ ነው። ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት

የሆነችው በህዝ ህብረት ነው። የህዝባችን ብዛት የጋራ ገበያ ሲሆን የኣገራችን ስፋት የልዩ ልዩ ሃብት ምንጭ ነው። ፌደራል ስርዓቱ ኣብዛኞቹ የተደራጁ፣ መንግስታዊ ስልጣን የያዙ የብሄሮች ምሁራን ስለሚደግፉት በኣጭር ጊዜ የሚነቃነቅ ኣይደለም፣ በቋንቋ ላይ የተመሰርቱ ክፍለ ሃገሮች መኖራቸው ምሁራን ከተስማሙበት የመጣላት ምክንያት መሆን የለበትም። መገንጠል

ለማንም ኣይጠቅምም ኣያስፈልግም።

ህዝባችን የረዥም ዘመናት ስርዓትን የማክበር ልምድ ስላለው መንግስት ከፈለገ በቀላሉ ስርዓትን፣ የህግ የበላይነትንና ሰላምን ማስከበር ይችላል፣ ማስከበርም ኣለበት።

ሰውን ማክበርና ህግን ማከበር ይደጋገፋሉ፣ ኣንድነታችን ይጠነክራል።

ሓምሌ 2011

 

 

Previous Story

የዝንጀሮ ቆንጆ! (በላይነህ አባተ)

Next Story

Deep History of The United States

Go toTop