“የትግራይ ክልል መንግስት አዝዞ ነው”

January 9, 2019

በወልቃይት አካባቢ በዛሬማ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘው የዛሬማ ሜይዴይ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ለስቲዲዮ ጋሊ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅትና ለኤፈርቱ ሱር ኮንስትራክሽን በህገ ወጥ መንገድ መሰጠቱን በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=pKU8igiCV3I&t=500s
ፕሮጀክቱ ሲጀመር 4 ቢሊዮን 180 ሚሊዮን ብር ነው ተብሎ የተያዘለት በጀት ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ በ347.7 ፐርሰንት ጨምሮ ወደ ብር 14 ቢሊዮን 533 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ማድረጉንና የ10 ቢሊዮን 353 ሚሊዮን ብር ልዩነት እንደተገኘበት በኦዲት ግኝቱ አስረድቷል
በኦዲት ግኝቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የውሃ፣መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኢታ ዶ/ር አብረሃም አዱኛ የዛሬማ ሜይዴይ የመስኖ ግድብ ግንባታ በስኳር ኮርፖሬሽን የተጀመረ መሆኑን በመግለፅ በቂ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ለሕወሓቱ ሱር ከንስትራክሽን እንዲሰጥ የተደረገበት ምክንያት የትግራይ ክልል መንግስት አዝዞ ነው ብለዋል::

Previous Story

ሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ ጣቢያዋን ለመሸጥ እየተደራደረች ነው

Next Story

ባህርዳር ከተማ ሁለት ዓይነት የተቃውሞ ሰልፎችን አስተናግዳለች

Go toTop