ከኤርትራ ድንበር ጓዙን ጠቅልሎ ሲሄድ ሕወሓት ባደራጃቸው የትግራይ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶበት የነበረው መከላከያው በሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ቀጭን ትእዛዝ መንገድ አስከፍቶ ወደ ተላከበት መንቀሳቀሱን የመከላከያ ምንጮች ገለጹ:: ሰኞ ዕለት መንገድ ተዘግቶባቸው ሕዝቡ ማብራሪያ ጠይቆ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን መከላከያው ማክሰኞ ጠዋት መንገዱን አስከፍቶ ሲሄድ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ምንም ችግር እንዳልገጠመው ሰምተናል::
https://www.youtube.com/watch?v=yJGl1PI8qiY
ከዛላምበሳ ግምባር የጦር መሳሪያ ጭነው ወደ መሀል ሀገር ሲንቀሳቀሱ የታገቱ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች ተለቀዋል በሚል በሕወሓት ሰዎች በኩል የሚነዛው ወሬ የመከላከያ ሰራዊቱን አቅም ለማሳነስ መሆኑን የጠቆሙት እነዚሁ ምንጮች የመከላከያ ተሽከርካሪዎቹ መንገዱን አስከፍተው ነው የሄዱት ብለውናል::