ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በቁጥር 56 ዕትሟ በውስጧ የያዘቻቸውን ቁምነገሮች እናስቃኛችሁና ለማንበብ ፎቶ ግራፉ ላይ ይጫኑ።
ያው ጋዜጣችን መሠረቷ ሚኒሶታ ላይ በመሆኑ በፊት ገጾቻችን በሚኒሶታ እየተካሄዱ ያሉው ወቅታዊ ሁኔታዎችን ዘግበናል።
– በሚኒሶታ ኦክቶበር 27 አዳዲስ የኮሜዲ ሥራዎችን ይዘው የሚመጡት ክበበው ገዳ፣ መስከረም በቀለና ት ዕግስት ንጋቱ ““ወደሚኒሶታ የምንመጣው አዳዲስ ቀልዶችንና ድራማዎችን ይዘን ነው” ብለዋል። በተጨማሪም መስከረም በቀለ “- “ከሌላው ቦታ በተለየ የሚኒሶታ ሕዝብ ለኮሜዲዎች በጣም እንደሚስቅ ተረድተናል” – ይለናል ዘገባውን ከውስጥ እንመልከተው።
– በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ3 ወር በፊት 11 አባላት ብቻ እንዳሉት ከተዘገበ በኋላ ሕዝቡ በገፍ እየተመዘገበ ነው… የአባላት ቁጥር 254 ደርሷል፤ በሚኒሶታ ኢትዮጵያዊ አንድነት እያየለ መጥቷል… ዘገባውን ይመልከቱት..
– የፕ/ር አልማርያም አዲስ ጽሑፍ የቁጥር 56 ዕትማችን አካል ነው፦
* “ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት” ይሉናል ፕሮፌሰሩ – ያንብቡት።
– ከሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጋር በመተባበርም የማህበረሰብ ጤና ትምህርት በስትሮክ በሽታ ዙሪያ አንድ ዘገባ ይዘናል
– በከተማችን በሚገኙ የማህበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ጥያቄ መሠረት በዌብሳታችን ላይ አውጥተነው የነበረው የተመስገን ደሳለኝ “ቀጣዩ የኢሕ አዴግ ኢላማ ማህበረ ቅዱሳን?” የሚለው ዘገባንም ይዘናል
– በእንመካከር አምድ የ4 አንባቢያን ጥያቄ በዶ/ሮች ምላሽ አግኝተዋል፡
* ጓደኞቼ መጥፎ ሽታ ትሸተናለህ ይሉኛል፣ ሽታው ከየት የመጣ ነው?
* ራሴን ለማሻሻል በተደጋጋሚ እቅድ አወጣለሁ፤ ነገር ግን አልተገብረውም፤ ምን ትመክሩኛላችሁ?
* የሴት ጡት አለኝ ምንድን ነው ጉዱ?
* ‹‹የቆዳ ሽፍታና አስም ምን አገናኛቸው? ልጄም እንደኔ የአስም በሽተኛ ይሆንብኝ ይሆን?›› – ለነዚህ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች ከጋዜጣችን ውስጥ ተካቷል።
– የኛ ማህበረሰብ በአሜሪካ ጥቅሙን በደንብ ያልተረዳው የሕይወት ኢንሹራንስ (Life Insurance) – በመብት አምዳችን ላይ የተሰተናገደ
– ለወሩ ታላቅ ዜና አምዳችን የጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋን “ፈጠራ የሚመስሉ እውነታዎች” የሚለውን ትንታኔ መርጠናል””
– በጥበብ አምዳችን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ “ለኛ ደበበ እሸቱ የምንጊዜውም ምርጥ አርቲስታችን ነው” ሲሉ ያቀረቡት ወቅታዊ ጽሁፍ ተይዟል።
– ከወር ወር ሕዝብ በጉጉት በሚጠብቀው የጤና ገጾቻችን 4 ጉዳዮችን ይዘናል
* ዘ-ሐበሻና የሚኒሶታ የጤና ቢሮ በመተባበር በወቅታዊው የጉንፋን በሽታ ዙሪያ አንድ መረጃ ይዘናል
* አትክልት ተመጋቢ መሆን የእንስሳት ተዋፅኦዎችን ይተካል?
* የአስም ህክምናዎችና መድሃኒቶች በቀድሞዎቹ እና በአዳዲስ ጥናቶች ውስጥ
* የአጥንት ነገር! – አጥንቶቻችን ስንት ናቸው? – የአጥንት ስራ ምንድነው? – አጥንት ሲሰበር እንዴት ይኮናል?
– በሳይኮሎጂ አምዶቻችን 2 ጉዳዮችን በዚህ ወር እትማችን ይዘናል
* ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች
* ላፈቀርካት ሴት ያለህን የፍቅር ስሜት እንዴት መግለፅ ትችላለህ?
– በስፖርት አምዳችን 3 ጉዳዮች ተይዘዋል።
* ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ሰሞኑን በድረ ገጹ ያሰፈረው “ናይጄሪያ እኛን፤ እኛ ደግሞ ታሪካችንን አሸንፈናል” የሚለውን ጽሁፍ ለጋዜጣችን አንባቢዎች አካፍለናል
* አርሴን ቬንገርን ወደወጣትነታቸው የመለሰው ፍላሚኒ
* የሚኒሶታው ቫይኪንግ በዚህ ሲዝን
– በወንጀልና ምርመራ አምዳችን ላይ ባሌ ውስጥ ስለተፈጸመ የግድያ ታሪክ የሚያወጋ ጽሁፍ ይዘናል
ምን ይሄ ብቻ?….. በቁጥር 56 እትማችን ብዙ ነግሮች ከማስታወቂያዎች ጋር ታጅበው ቀርበዋል ያንብቡ፤ ያካፍሉ።