የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት በሚያደርገው ሕዝባዊ ትግል፣ በውጭ አገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በልዩ ልዩ ሕዝባዊ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ዙርያ በመደራጀት በወሳኝ ትግል ውስጥ መሳተፍ ከጀመርን በርካታ ዓመታት አሳልፈናል።
በነዚህ የትግል ግዜያቶች፣ በ አገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለው ሕብተረተሰብ ካቀረበልን አብይ ጥያቄ አነዱና ዋነኛው፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዐላዊነትና አነድነት ዙርያ ተሰባስበን በሕብረት እንድንታገል ነው።
ይህንን ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ ለመመለሰ በርካታ የፖለቲካ፣ የሲቪክ ድርጅቶችና አገር ወዳድ ግለሰቦችን ያቀፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ( ሸንጎ ) በመመስረት ድርጅቱ የቆመለትን ታሪካዊ ሓላፊነት እያከናወነ አንድ የጉባዔ ግዜ አሳልፏል። — ለሙ ጥሪው እዚህ ላይ ይጫኑ—
[gview file=”https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2013/10/sibseba-poster.pdf”]