በጎጃም ሶስት ወረዳዎች የሚኖሩ ሕዝቦች መንግስትን አስደነገጡ

October 12, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በጎጃም ጎንቻ ሲሶ፣ ሁለት እጁ እነብሴ እና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ሰሚ ያጣ ህዝብ በሚል መንግስት ጥያቄዎቻችንን ባስቸኳይ ካልመለሰልን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ በተለይ ነዋሪዎቹ ቢቸና፣ደጀን፣ሞጣ ባህርዳር ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ለማስራት ከዚህ ቀደም የሞቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ቃል ቢገቡም እስካሁን አልተሰራም፤ አሁን ደግሞ የመንገድ ግንባታው ተሰርዟል ተብለናል በሚል መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ማታ በወረዳዎቹ ከተሞች ላይ በራካታ መፈክሮች ያሉት ፖስተሮችን ለጥፈው አድረዋል ሲል የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ዘግቧል።

በደል የወለደው ቁጭት በሚል ርዕስ ግብር ያለልማት ብዝበዛ ነው፣አንድ መንግስት መንገድ ለመስራት ስንት ዓመት ይፈጅበታል፣ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በርካት ጥያቄዎችንም ማንሳታቸው ታውቋል፡፡ይህንም የአካባቢው አመራሮች መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አይተው በመደናገጥ ፖስተሮችን ያስቀደዱ ሲሆን፤ ህዝቡ አሁንም ጥያቄያችን ካልተመለሰ በአካባቢያችን ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ ሶቆችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተዘግተው የተቃውሞ ሰልፍ እንወጣለን ሲሉ በማስጠንቀቃቸው እስካሁንም በአካባቢው ውጥረቱ አይሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ የአካባቢውን ባለስልጣናት ዘሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

Previous Story

የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካ የሚገኙትን አቶ ስብሃት ነጋን አፋጠጣቸው ድምፃችን ይሰማ …..

Next Story

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው – ከኢየሩሳሌም አረአያ

Go toTop