በሙስና ከታሰሩ ባለስልጣናት መካከል የተወሰኑት ስም ዝርዝር ታወቀ | ይዘነዋል (Updated)

July 26, 2017

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶችና ደላሎች፤ በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ::

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ 34 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና ደላሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ኃላፊዎቹ ተጠርጥረው የተያዙት “በፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግና በፌደራልና አዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በተደረገ የማጣራት ስራ የሙስና ተግባር ውስጥ ተሳትፈው በመገኘታቸው መንግስት ሙስናን ለመከላከል በያዘው ቁርጠኛ አቋም ነው፤” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል::

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ  ኃላፊዎች ከተገኙባቸው የመንግስት  ተቋማት መካከል፤ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ ስኳር ኮርፖሬሽን እና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ጋር ይገኙበታል፡፡

ማክሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. መንግሥት እምነት በማጉደልና ሥልጣንን ያላግባብ በመገልገል በአገር ላይ ከ1.15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ያላቸው ተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን

  1. ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ
  2. ኢንጂነር ዋሲሁን
  3. ኢንጂነር አህመዲን
  4. ሚስተር ሚናሽ ሌቪ (ትህዳር ኮንስትራክሽን ኩባንያ)

(ከ198 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

  1. አቶ አብዶ መሐመድ
  2. አቶ በቀለ ንጉሤ
  3. አቶ ገላና ቦሪ
  4. አቶ የኔነህ አሰፋ
  5. አቶ በቀለ ባልቻ
  6. አቶ ገብረ አናንያ ፃዲቅ

(ከ646 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ

  1. አቶ እንዳልካቸው ግርማ
  2. ወ/ሮ ሰናይት ወርቁ
  3. አቶ አየነው አሰፋ
  4. አቶ በለጠ ዘለለው

(ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር

  1. አቶ ሙሳ መሐመድ
  2. አቶ መስፍን ወርቅነህ
  3. አቶ ዋሲሁን አባተ
  4. አቶ ሥዩም ጎበና
  5. አቶ ታምራት አማረ
  6. አቶ አክሎግ ደምሴ
  7. አቶ ጌታቸው ነገራ
  8. ዶ/ር ወርቁ አብነት (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)
  9. አቶ ታመነ ደባልቄ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)
  10. አቶ ዮናስ መርአዊ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)

(2.2 ሚሊዮን ዶላር ወይም 51.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ)

ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

  1. አቶ አበበ ተስፋዬ
  2. አቶ ቢልልኝ ጣሰው

(ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

  1. አቶ አበበ ተስፋዬ
  2. አቶ የማነ ግርማይ (ጂዋይቢ ኮንስትራክሽን ኩባንያ)
  3. አቶ ዳንኤል አበበ

(ከ20 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)

  1. አቶ ፈለቀ ታደሰ
  2. አቶ ኤፍሬም ታደሰ

(ከ10 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)

ኦሞ ኩራዝ ስኳር ቁጥር 5 ፋብሪካ

  1. አቶ መስፍን መልካሙ
  2. አቶ ሰለሞን ከበደ
  3. ሚስተር ሊዮ (የቻይና ጁጂአይሺኢ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ)
  4. አቶ ፀጋዬ ገብረ እግዚአብሔር ብርሃነ
  5. ወ/ሮ ሳሌም ከበደ

(ከ184 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

Previous Story

በብዕር ስም የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶቹን ማን ነዉ እያሲያዛቸዉ ያለዉ? – ሸንቁጥ አየለ

Next Story

ከደጋጎቹ ጠበቆች መካከል አንዱ

Go toTop